am_luk_text_ulb/10/17.txt

1 line
796 B
Plaintext

\v 17 ሰባዎቹም ደስ እያላቸው ተመለሱና፡- ‹‹ጌታ ሆይ፣ አጋንንት እንኳን በስምህ ታዘዙልን›› አሉት፡፡ \v 18 ኢየሱስም፡- ‹‹ሰይጣን እንደ መብረቅ ከሰማይ ሲወድቅ እየተመለከትኩ ነበር፡፡ \v 19 አስተውሉ፣ በእባቦችና በጊንጦች ላይ ትረማመዱ ዘንድ በጠላትም ኃይል ሁሉ ላይ ሥልጣንን ሰጥቻችኋለሁ፣ በምንም ዓይነት መንገድ ምንም አይጐዳችሁም፡፡ \v 20 ይሁን እንጂ መናፍስት ስለተገዙላችሁ በዚህ ብቻ ደስ አይበላችሁ፣ ነገር ግን ስሞቻችሁ በሰማይ የተጻፉ በመሆናቸው በዚህ የላቀ ደስታ ይሰማችሁ፡፡