am_luk_text_ulb/12/37.txt

1 line
606 B
Plaintext

\v 37 በሚመጣበት ጊዜ ነቅተው ሲጠብቁ ጌታቸው የሚያገኛቸው እነዚያ አገልጋዮች የተመሰገኑ ናቸው፡፡ በእርግጥ እነግራችኋለሁ፣ እሱም የሥራ ልብሱን ለብሶ ምግብ ለመመገብ እንዲቀመጡ ያደርጋቸውና ወደ እነርሱ ዘንድ መጥቶ ያገለግላቸዋል፡፡ \v 38 ከሌሊቱ በስድስት ሰዓት ወይም በዘጠኝ ሰዓትም እንኳን ቢሆን ሲመጣ ተዘጋጅተው የሚያገኛቸው እነዚያ አገልጋዮች የተመሰገኑ ናቸው፡፡