am_luk_text_ulb/07/24.txt

1 line
722 B
Plaintext

\v 24 \v 25 \v 26 24-26 የዮሐንስ መልእክተኞች ከሄዱ በኋላ ኢየሱስ ዮሐንስን በሚመለከት እንዲህ አላቸው፦ “ወደ ምድረ በዳ የወጣችሁት በንፋስ የሚወዛወዘውን ሸንበቆ ለማየት ነበርን? ወይስ የወጣችሁት የሚያማምሩ ልብሶች የለበሱትን ለማየት ነበርን? አስተውሉ፣ የሚያማምሩ ልብሶችን ለብሰው በድሎት የሚኖሩ ሰዎች የሚገኙት በቤተ መንግሥታት ነው። ልታዩ የወጣችሁት ግን ነቢይ ከሆነ፣ እንግዲያውስ ያያችሁት ነቢይ ብቻ ሳይሆን ከነቢያትም የበለጠውን ነው።