\v 47 ገና እየተናገረ እያለ ብዙ ሰዎች ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ የሆነው ይሁዳ እየመራቸው መጡ። ይሁዳም ሊስመው ወደ ኢየሱስ ቀረበ፤ \v 48 ነገር ግን ኢየሱስ፣ “ይሁዳ ሆይ፣ የሰውን ልጅ በመሳም አሳልፈህ ትሰጣለህን?” አለው።