am_luk_text_ulb/12/51.txt

1 line
638 B
Plaintext

\v 51 በምድር ሰላምን ለማምጣት እንደመጣሁ ታስባላችሁን? እንደዚያ አታስቡ፣ እነግራችኋለሁ፣ የመጣሁት ይልቁኑ መለያየትን ላመጣ ነው፡፡ \v 52 ከእንግዲህ ወዲህ በአንድ ቤት ውስጥ አምስት ሰዎች ቢኖሩ ሦስቱ በሁለቱ ላይ፣ ሁለቱም በሦስቱ ላይ የሚነሱና የሚለያዩ ይሆናሉ፡፡ \v 53 አባትዬው በልጅዬው ላይ ልጅዬውም በአባትዬው ላይ፤ አማትዬው በምራቷ ላይ፣ ምራቲቱም በአማትዋ ላይ ይነሡና ይለያያሉ፡፡