am_luk_text_ulb/23/08.txt

1 line
579 B
Plaintext

\v 8 ሄሮድስ ኢየሱስን ባየው ጊዜ በጣም ደስ አለው፣ ምክንያቱም ለረጅም ጊዜ ሊያየው ሲፈልግ ነበር። ስለ እርሱ ሰምቶ የነበረ ሲሆን፣ አንዳንድ ተአምራት ሲያደርግ ለማየትም ተስፋ ነበረው። \v 9 ሄሮድስ ኢየሱስን በብዙ ቃሎች ቢጠይቅም፣ ኢየሱስ ግን ምንም መልስ አልሰጠውም። \v 10 በዚህ ጊዜ የካህናት አለቆችና የሕግ መምህራን ተነሥተው ቆሙና በኅይለ ቃል ከሰሱት።