\v 6 ሁለት ድንቢጦች በሁለት ዝቅተኛ ዋጋ ያላቸው ሳንቲሞች ይሸጡ የለምን? ይሁን እንጂ ከእነርሱ አንዷም እንኳ በእግዚአብሔር ዘንድ የተዘነጋች አይደለችም፡፡ \v 7 ነገር ግን የእናንተ የራሳችሁ ፀጉሮች እንኳ የተቆጠሩ ናቸው፡፡ አትፍሩ፣ እናንተ ከብዙ ድንቢጦች የላቀ ዋጋ አላችሁ፡፡