am_luk_text_ulb/09/07.txt

1 line
693 B
Plaintext

\v 7 \v 8 \v 9 7 እየተደረገ የነበረውን ሁሉ በሰማ ጊዜ የአራተኛው ክፍል ገዢ ሄሮድስ በጣም ተሸበረ፣ ምክንያቱም ‘አንዳንዶቹ መጥምቁ ዮሐንስ ከሞት ተነሥቷል፣ 8 በሌሎች ዘንድ ደግሞ ኤልያስ ተገልጧል፣ እንደገና ሌሎች ከጥንት ነቢያት አንዱ ሕያው ሆኖ ተነሥቷል’ እንደሚሉ ሰምቷል። 9 ሄሮድስም “የዮሐንስን ራስ እኔ አስቆርጬዋለሁ፣ እንዲህ ያለ ነገር የምሰማበት ይሄ ማን ነው?” አለ። ኢየሱስንም ለማየት ሄሮድስ ጥረት ያደርግ ነበር።