\v 33 ጴጥሮስ፣ “ጌታ ሆይ፣ ወደ እስር ቤትም ይሁን ወደ ሞት ከአንተ ጋር ለመሄድ ዝግጁ ነኝ” አለው። \v 34 ኢየሱስ፣ “ዛሬ ዶሮ ሳይጮኽ አላውቀውም ብለህ ሦስት ጊዜ እንደምትክደኝ እነግርሃለሁ” ብሎ መለሰለት።