\c 22 \v 1 ፋሲካ የተባለው የቂጣ በዓል ተቃርቦ ነበር። \v 2 የካህናት አለቆችና የሕግ መምህራን ሕዝቡን ይፈሩ ስለ ነበር፣ ኢየሱስን እንዴት አድርገው እንደሚገድሉት ተመካከሩ።