am_luk_text_ulb/16/19.txt

1 line
523 B
Plaintext

\v 19 ኢየሱስ እንዲህ አለ፤ "ሐምራዊና ቀጭን የሐር ልብስ የለበሰ በየቀኑም በምቾትና በደስታ የሚኖር ሀብታም ሰው ነበረ። \v 20 ሰውነቱ በቊስል የተወረረ አልዓዛር የሚባል ለማኝም በሀብታሙ ሰው ደጅ ይተኛ ነበር። \v 21 አልዓዛርም ከሀብታሙ ማዕድ የተረፈውን ፍርፋሪ ሊመገብ ይመኝ ነበር። ውሾች እንኳ እየመጡ ቊስሉን ይልሱ ነበር።