am_luk_text_ulb/10/13.txt

1 line
651 B
Plaintext

\v 13 ወዮልሽ ኮራዚን! ወዮልሽ ቤተ ሳይዳ! በእናንተ ዘንድ የተደረጉት ታላላቅ ታምራት በጢሮስና በሲዶና ተደርገው ቢሆን ኖሮ፣ የሐዘን ልብስ ለብሰውና ራሳቸውን አዋርደው ከረጅም ጊዜ በፊት ንስሐ በገቡ ነበር፡፡ \v 14 ነገር ግን በፍርድ ወቅት ከእናንተ ይልቅ ለጢሮስና ለሲዶና ይቀልላቸዋል። \v 15 አንቺስ ቅፍርናሆም፣ እስከ ሰማይ ከፍ እንዳልሽ ታስቢ ይሆን? እንደዚያ አታስቢ፣ እስከ ሲዖል ድረስ ትወርጃለሽ።