am_luk_text_ulb/06/17.txt

1 line
759 B
Plaintext

\v 17 ከዚያ በኋላም ኢየሱስ ከተራራው ወረደና በደልዳላ ቦታ ላይ ቆመ፡፡ ከደቀመዛሙርቱ በርከት ያሉት፣ ከይሁዳና ከኢየሩሳሌም እንዲሁም ከጢሮስና ከሲዶና ባሕር ዳርቻ ብዙ ሰዎች በዚያ ነበሩ፡፡ \v 18 ወደዚያ የመጡት እርሱን ሊያዳምጡትና ከበሽታዎቻቸው ሊፈወሱ ነበር፡፡ በርኩሳን መናፍስት ሲጨነቁ የነበሩም ሰዎች ተፈወሱ፡፡ \v 19 የሚፈውስ ኃይል ከእርሱ ይወጣ ስለነበረ፣ በሕዝቡ መካከል ያለ እያንዳንዱ ሰው እርሱን ለመንካት ጥረት ያደርግ ነበር፤ እርሱም ሁሉንም ፈወሳቸ.