\v 10 ከዚያም እንዲህ አላቸው፣ "ሕዝብ በሕዝብ ላይ ይነሣል፣ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣል። \v 11 ታላቅ የመሬት መንቀጥቀጥ ይሆናል፣ ደግሞም በተለያዩ ቦታዎች ራብና ቸነፈር ይከሠታል። አስፈሪ ሁነቶችና ታላላቅ ምልክቶች ከሰማይ ይገለጣሉ።