\v 43 በዚያም ለዐሥራ ሁለት ዓመት ደም ሲፈሳት የነበረች፣ ገንዘቧን ሁሉ ለሐኪሞች ብትከፍልም አንዳቸውም ያልፈወሷት አንዲት ሴት ነበረች። \v 44 እርሷ ከኢየሱስ በስተኋላ መጥታ የልብሱን ጫፍ ነካች፤ የፈሳት የነበረው ደምም ወዲያው ቆመ።