\v 35 ኢየሱስ ወደ ኢያሪኮ በቀረበ ጊዜ፤ አንድ ዐይነ ስውር ምጽዋት እየለመነ በመንገድ ዳር ተቀምጦ ነበር። \v 36 እርሱም በአጠገቡ የሚያልፉትን የብዙ ሰዎች ድምጽ በሰማ ጊዜ ፦ " ምን እየሆነ ነው?"ብሎ ጠየቃቸው። \v 37 እነርሱም፦ " የናዝሬቱ ኢየሱስ በዚህ በኩል እያለፈ ነው" ብለው ነገሩት።