\v 23 ጌታውም አገልጋዩን፣ 'ወደ ጎዳናዎችና ወደ ገጠር መንገዶች ውጣ፤ ቤቴም እንዲሞላ ያገኘሃቸውን ሁሉ እንዲገቡ ግድ በላቸው። \v 24 "እላችኋለሁ፣ በመጀመሪያ ከተጋበዙት ከእነዚያ ሰዎች መካከል አንድ ሰው እንኳ ከእራቴ አይቀምስም' አለው።