\v 25 እነሆ፣ አንድ የአይሁድ ሕግ መምህር ሊፈትነው ፈልጎ ብድግ አለና፡- ‹‹መምህር ሆይ፣ የዘላለምን ሕይወት ለመውረስ ምን ማድረግ ይገባኛል?›› በማለት ጠየቀው፡፡ \v 26 ኢየሱስም፡- ‹‹በሕጉ የተጻፈው ምንድን ነው? የተረዳኸው እንዴት ነው?›› አለው። \v 27 እርሱም፡- ‹‹ጌታ አምላክህን በሙሉ ልብህ፣ በሙሉ ነፍስህ፣ በሙሉ ኃይልህ፣ በሙሉ ዐሳብህም ውደድ እንደዚሁም ባልንጀራህን እንደ ራስህ አድርገህ ውደድ›› ብሎ መለሰ፡፡ \v 28 ኢየሱስም፡- ‹‹በትክክል መልሰሃል፡፡ ይህን አድርግ በሕይወትም ትኖራለህ›› አለው፡፡