\v 16 የመጀመሪያው አገልጋይ ወደፊቱ ቀረበና፣ 'ጌታ ሆይ፣ ምናንህ ተጨማሪ ዐሥር ምናን አትርፎልሃል' አለው። \v 17 ጌታውም፣ “ደግ አድርገሃል፣ አንተ ታታሪ አገልጋይ። በጥቂቱ ስለ ታመንህ፣ በዐሥር ከተሞች ላይ ገዥ ትሆናለህ' አለው።