\v 13 ከሕዝቡም መካከል አንድ ሰው፡- ‹‹መምህር ሆይ፣ ወንድሜ ርስት እንዲያካፍለኝ ንገረው›› አለ፡፡ \v 14 ኢየሱስም፡- ‹‹አንተ ሰው፣ በእናንተ ላይ ዳኛ ወይም አደራዳሪ አድርጎ የሾመኝ ማን ነው?›› አለው፡፡ \v 15 ለእነርሱም እንደዚህ አላቸው፡- ‹‹ስግብግብነት ከሞላባቸው ምኞቶች ራሳችሁን ጠብቁ፣ ምክንያቱም የአንድ ሰው ሕይወት በሀብቱ ብዛት ላይ የተመሠረተ አይደለም››