\v 42 42 ነገር ግን እናንተ ፈሪሳውያን ወዮላችሁ፤ ምክንያቱም ካመረታችሁት አዝሙድና ጤና አዳም አሥራት እያወጣችሁ ፍትሕንና የእግዚአብሔርን ፍቅር ንቃችሁ ትተዋላችሁ። ሌላውን ነገር ማድረግ ሳትተዉ ፍትሕ ማድረግንና የእግዚአብሔርን ፍቅር መጠበቅ ያስፈልጋችኋል።