\v 41 ጴጥሮስም እንደዚህ አለ፡- ‹‹ጌታ ሆይ፣ ይህንን ምሳሌ የተናገርከው ለእኛ ብቻ ነው ወይስ ለሌሎችም ሰዎች ሁሉ ነው?›› \v 42 ጌታም እንደዚህ አለ፡- ‹‹ታዲያ ለሌሎቹ አገልጋዮቹ የተመደበላቸውን ምግብ በትክክለኛው ጊዜ ይሰጣቸው ዘንድ ጌታው የሾመው ታማኝና ብልህ አስተዳዳሪ ማን ነው? \v 43 በሚመጣበት ጊዜ ይህንን ሲያደርግ ጌታው የሚያገኘው ያ አገልጋይ የተመሰገነ ነው፡፡ \v 44 በእርግጥ እነግራችኋለሁ፣ ባለው ንብረት ሁሉ ይሾመዋል፡፡