\v 54 ያዙትና ወሰዱት፣ ወደ ሊቀ ካህናቱ ቤትም አመጡት። ጴጥሮስ ግን ከርቀት ተከተለው። \v 55 በግቢው መሓል እሳት ካቀጣጠሉና ዐብረው ከተቀመጡ ጴጥሮስ መጥቶ በመካከላቸው ተቀመጠ።