\c 21 \v 1 ኢየሱስ ቀና ብሎ ሲመለከት ሀብታም ሰዎች በመባ መሰብሰቢያ ሣጥን ውስጥ ገንዘብ ሲጨምሩ አየ። \v 2 አንዲት ድኻ መበለት ደግሞ ሁለት ሳንቲሞችን ስትጨምር አየ። \v 3 ስለዚህ እንዲህ አለ፣ "እውነት እላችኋለሁ፣ ይህች ድኻ መበለት ከሁሉም የበለጠ ሰጠች። \v 4 እነዚህ ሁሉ የሰጡት ስጦታ ከተትረፈረፈ ሀብታቸው ነው። ይህች መበለት ግን በድኽነቷ መተዳደሪያዋን ሁሉ ሰጠች።"