am_lev_text_ulb/05/07.txt

1 line
858 B
Plaintext

\v 7 ጠቦት መግዛት ካልቻለ፣ ለኃጢአቱ የበደል መስዋዕት ለያህዌ ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት እርግቦች ማምጣት ይችላል፤ አንዱ ለኃጢአት መስዋዕት እና ሌላኛው ለሚቃጠል መስዋዕት ያመጣል፡፡ \v 8 እነዚህን ወደ ካህኑ ያመጣል፣ እርሱም በመጀመሪያ አንዱን ለኃጢአት መስዋዕት ያቀርባል - እርሱም የመስዋዕቱን ራስ ከአንገቱ ይቆለምማል ነገር ግን ሙሉ ለሙሉ አይለያየውም፡፡ \v 9 ከዚያ ከኃጢአት መስዋዕቱ ጥቂት ደም ወስዶ በመሰዊያው ጎን ይረጫል፣ ከዚያ የቀረውን ደም በመሰዊያው ስር ደሙን ያንጠፈጥፈዋል፡፡ ይህ የኃጢአት መስዋዕት ነው፡፡