am_lev_text_ulb/04/01.txt

1 line
716 B
Plaintext

\c 4 \v 1 ያህዌ ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፣ \v 2 “ለእስራኤል ህዝብ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፣ ‘ማንም ሰው ያህዌ እንዳይደረግ ያዘዘውን ማናቸውንም ነገር በማድረግ ኃጢአት መስራት ሳይፈልግ ኃጢአት ቢሰራ፣ ደግሞም የተከለከለ አንዳች ነገር ቢያደርግ፣ እንዲህ ይደረግ፡፡ \v 3 ኃጢአት የሰራው ሊቀ ካህኑ ቢሆንና በህዝቡ ላይ በደል የሚያስከትል ኃጢአት ቢሰራ ስለ ሰራው ኃጢአት ለያህዌ ነውር የሌለበት ወይፈን የኃጢአት መስዋእት አድርጎ ያቅርብ፡፡