am_lev_text_ulb/10/08.txt

1 line
640 B
Plaintext

\v 8 ያህዌ አሮንን እንዲህ አለው፣ \v 9 “አንተ፣ ወይም ከአንተ ጋር የሚሆኑ ልጆችህ ወደ መገናኛው ድንኳን ስትገቡ እንዳትሞቱ ወይን ጠጅ ወይም የሚያሰክር መጠጥ አትጠጡ፡፡ ይህ በትውልዳችሁ ሁሉ ቋሚ ስርዓት ይሆናል፣ \v 10 ቅዱስ በሆነውና ተራ በሆነው መሃል ለመለየት፣ ንጹህ በሆነውና ንጹህ ባልሆነው መሃል ለመለየት፣ \v 11 ለእስራኤል ህዝብ ሁሉ በሙሴ በኩል ያህዌ ያዘዘውን ስርዓት ሁሉ አስተምሩ፡፡”