Tue May 16 2017 11:16:07 GMT+0300 (E. Africa Standard Time)

This commit is contained in:
burje_duro 2017-05-16 11:16:15 +03:00
commit aceffacda8
573 changed files with 629 additions and 0 deletions

1
00/title.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
Jeremiah

1
01/01.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 1 ይህ የኬልቅያስ ልጅ የሆነው የኤርምያስ ቃል ነው፤ እርሱ በብንያም ምድር ከነበሩት ካህናት አንደኛው ነበር። \v 2 የአሞጽ ልጅ በሆነው በይሁዳ ንጉሥ ዐሥራ ሦስተኛ ዓመት አገዛዝ ዘመን ላይ የእግዚአብሔር ቃል ወደ እርሱ መጣ። \v 3 ቃሉ የመጣው በይሁዳ ንጉሥ የኢዮስያስ ልጅ በሆነው ኢዮአቄም ዘመን፣ የኢዮስያስ ልጅ በሆነው የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ የዐሥራ አንደኛው አመት አገዛዝ አምስተኛ ወር ድረስ፣ የኢየሩሳሌም ሕዝቦች ምርኮኛ ሆነው ሲወሰዱ ነበር።

1
01/04.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 4 የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፣ \v 5 "በማኅፀን ሳልሠራህ አውቄሃለሁ፥ ከማኅፀንም ሳትወጣ ቀድሼሃለሁ፥ ለአሕዛብ ነቢይ አድርጌሃለሁ።" \v 6 እኔም፣ "ወዮ ጌታ እግዚአብሔር፥ ገና ብላቴና በመሆኔ እንዴት እንደምናገር አላውቅም" አልሁ።

1
01/07.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 7 ነገር ግን እግዚአብሔር "'ገና ብላቴና ነኝ' አትበል። ወደምልክህ ሁሉ ልትሄድ ይገባል፣ የማዝዝህንም ሁሉ ልትናገር ይገባል! \v 8 ላድንህ ከአንተ ጋር ስለሆንኩ አትፍራ - ይህ የእግዚአብሔር ንግግር ነው።" አለኝ።

1
01/09.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 9 እግዚአብሔርም እጁን ዘርግቶ አፌን ዳሰሰ፣ እንዲህም አለኝ "ቃሌን በአፍህ ውስጥ አኑሬአለሁ፤ \v 10 ትነቅልና ታፈርስ ዘንድ፥ ታጠፋና ትገለብጥ ዘንድ፥ ትሠራና ትተክል ዘንድ በአሕዛብና በመንግሥታት ላይ ዛሬ ሾሜሃለሁ" አለኝ።

1
01/11.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 11 የእግዚአብሔር ቃል "ኤርምያስ ሆይ፥ ምን ታያለህ?" እያለ ወደ እኔ መጣ። እኔም "የለውዝ በትር አያለሁ" አልሁት። \v 12 እግዚአብሔርም "መልካም አይተሃል፣ እፈጽመው ዘንድ በቃሌ እተጋለሁና" አለኝ።

1
01/13.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 13 የእግዚአብሔር ቃል ለሁለተኛ ጊዜ "ምን ታያለህ?" እያለ ወደ እኔ መጣ። እኔም "ፊቱ ከሰሜን አቅጣጫ የሆነ የሚፈላ ማሰሮ አያለሁ" አልሁ። \v 14 እግዚአብሔርም "በዚህች ምድር በሚኖሩት ሁሉ ላይ ከሰሜን አቅጣጫ ክፉ ነገር ይገለጣል" አለኝ።

1
01/15.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 15 በሰሜን ያሉትን የመንግሥታትን ወገኖች ሁሉ እጠራለሁና ይላል እግዚአብሔር። እነርሱም ይመጣሉ፣ እያንዳንዳቸውም በኢየሩሳሌም መግቢያ በራፍ ላይ፣ በዙሪያዋ ባሉት በአጥሮቿ ሁሉ ላይ፣ በይሁዳም ከተሞች ሁሉ ላይ ዙፋናቸውን ያኖራሉ። \v 16 እኔን ስለተዉበት ክፋታቸው ሁሉ፣ ለሌሎችም አማልክት ስላጠኑ፣ በገዛ እጃቸው ለሠሯቸውም ስለሰገዱላቸው፣ ፍርዴን በእነርሱ ላይ እናገራለሁ።

1
01/17.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 17 አንተ ራስህን አዘጋጅ! ተነሥና ያዘዝሁህን ሁሉ ንገራቸው። በእነርሱ ፊት አትፍራ፣ አሊያ እኔ በእነርሱ ፊት አስፈራሃለሁ! \v 18 ተመልከት! ዛሬ በምድሪቱ ሁሉ ላይ በይሁዳም ነገሥታት -በአለቆችዋና በካህናትዋ ላይ በምድሪቱም ሕዝብ ላይ እንደ ተመሸገ ከተማ እንደ ብረትም ዓምድ እንደ ናስም ቅጥር አድርጌሃለሁ። \v 19 ይዋጉሃል፣ ነገር ግን አድንህ ዘንድ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አያሸንፉህም" ይላል እግዚአብሔር።

1
02/01.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 1 የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ መጣ፣ እንዲህም አለኝ፣ \v 2 "ሂድና በኢየሩሳሌም ጆሮ ጩኽ። እንዲህም በል 'እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በወጣትነትሽ የነበረሽን የኪዳን ታማኝነት፣ በታጨሽበት ጊዜ የነበረሽን ፍቅር፣ ዘር ባልተዘራበት ምድረ በዳ እንደ ተከተልሽኝ ስለአንቺ አስታውሳለሁ። \v 3 እስራኤል ለእግዚአብሔር ቅዱስ ነበረ፣ የእርሻው መከር በኩራትም ነበረ! ከበኩራቱ የበሉት ሁሉ ኃጢአት አድርገዋል! ክፉም ነገር ይመጣባቸዋል ይላል እግዚአብሔር።'"

1
02/04.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 4 የያዕቆብ ቤትና የእስራኤልም ቤት ቤተሰቦች ሁሉ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ። \v 5 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "አባቶቻችሁ ምን ክፋት አግኝተውብኝ ነው እኔን ከመከተል የራቁት፣ ከንቱ ጣዖታትንም የተከተሉት፣ እና ራሳቸውም ከንቱ የሆኑት? \v 6 እነርሱም 'ከግብጽ ምድር ያወጣን እግዚአብሔር፣ በምድረ በዳ ጉድጓድ ወዳለበት የአረባህ ምድር፣ በውኃ ጥምና በሞት ጥላ ምድር፥ ማንም በማያልፍበትና ማንም በማይቀመጥበት ምድር የመራን እግዚአብሔር ወዴት አለ?' አላሉም።

1
02/07.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 7 ነገር ግን ፍሬዋንና ሌሎች መልካም ነገሮቿን እንድትበሉ ወደ ቀርሜሎስ ምድር አገባኋችሁ! ይሁን እንጂ በመጣችሁ ጊዜ፣ ምድሬን አረከሳችሁ፣ ርስቴንም አጐሳቈላችሁ! \v 8 ካህናቱም 'እግዚአብሔር ወዴት አለ? አላሉም፥ ባለ የኦሪቶች ሊቅ የሆኑትም ስለ እኔ ግድ አላላቸውም! እረኞችም በደሉኝ፥ ነቢያትም ለበኣል ትንቢት ተናገሩ፣ ትርፍ የሌለውንም ነገር ተከተሉ።

1
02/09.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 9 ስለዚህ እከስሳችኋለሁ - የልጆቻችሁንም ልጆች እከስሳለሁ። \v 10 ወደ ኪቲም ደሴቶች እለፉና ተመልከቱ። ወደ ቄዳርም መልእክተኞችን ላኩና እንደዚህ ያለ ነገር ህኖ እንደ ሆነ መርምራችሁ እዩ። \v 11 አማልክት ባይሆኑ እንኳን አማልክት ያልሆኑትን አማልክቱን የለወጣቸው አንድ ሕዝብ አለን? ነገር ግን ሕዝቤ ሊረዳቸው ለማይችለው ነገር ክብሩን ለወጠ።

1
02/12.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 12 ሰማያት ከዚህ የተነሣ ተደነቁ! ተንቀጥቀጡ እና ደንግጡ ይላል እግዚአብሔር። \v 13 ሕዝቤ ሁለቱን ክፉ ነገሮች በእኔ ላይ አድርገዋልና፦ ውሃ ለመያዝ የማይችሉትን የተቀደዱ ጉድጓዶች ለራሳቸው በመቆፈር እኔን የሕያውን ውኃ ምንጭ ትተውኛል!

1
02/14.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 14 እስራኤል ባርያ ነውን? ወይስ በቤት የተወለደ አይደለምን? እናስ ብዝበዛ የሆነው ለምንድነው? \v 15 የአንበሳ ደቦሎች በእርሱ ላይ አገሡ። ብዙ ድምጽ በማሰማት ምድሩን አስፈሪ አደረጉት! ከተሞቹም የሚኖርባቸው እንዳይኖር ሆኖ ተደመሰሰ። \v 16 የሜምፎስና የጣፍናስ ልጆች የራስ ቅልሽን ላጭተው ባርያዎችን ከአንቺ ወሰዱ! \v 17 ይህን ሁሉ በራስሽ ላይ ያደረግሽው በመንገድ ላይ ሲመራሽ አምላክሽን እግዚአብሔርን ስለተውሽ አይደለምን? ይላል እግዚአብሔር አምላክሽ።

1
02/18.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 18 አሁንስ በግብጽ መንገድ ሄደሽ የሺሖርን ውኃ የምትጠጪው ለምንድነው? በአሦርስ መንገድ ሄደሽ የኤፍራጥስንም ውኃ የምትጠጪው ለምንድነው? \v 19 ክፋትሽ ይገሥጽሻል፣ ክዳትሽም ይቀጣሻል፤ አምላክሽንም እግዚአብሔርን መተውሽ እኔንም መፍራት ማቆምሽ ክፉና መራራ ነገር እንደ ሆነ እወቂ፥ ተመልከቺ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።

1
02/20.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 20 ከጥንት ጀምሮ የነበረብሽን ቀንበር ሰብሬአለሁና፣ እስራትሽንም ቈርጫለሁ። እንዲህም ሆኖ አንቺ 'አላገለግልም!' አልሽ፥ ነገር ግን ከፍ ባለው ኮረብታ ሁሉ ላይ ከለምለምም ዛፍ ሁሉ በታች ተጋደምሽ፣ አንቺ አመንዝራ። \v 21 እኔ ራሴ ግን የተመረጠች ወይን፣ ፈጽሞ እውነተኛ የሆነ ዘር አድርጌ ተክዬሽ ነበር። አንቺ ግን ክፉ የእንግዳ ወይን ግንድ ሆነሽ እንዴት ተለወጥሽብኝ? \v 22 በወንዝ ብትታጠቢ ወይም በብርቱ ሳሙና ብትታጠቢ፣ በእኔ ፊት በኃጢአትሽ ረክሰሻል ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

1
02/23.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 23 'አልረከስሁም! በአሊምንም አልተከተልሁም' እንዴት ትያለሽ? በሸለቆዎች ያለውን ባህርይሽን ተመልከቺ! ያደረግሽውንም ተገንዘቢ፣ በመንገዷ ላይ እንደ ተለቀቀች ፈጣን ግመል ሆነሻል፤ \v 24 በምኞትዋ ከንቱ ነፋስን እንደምታሸትት፣ ምድረ በዳ እንደ ለመደች እንደ ሜዳ አህያ ነሽ! ከምኞትዋ የሚመልሳት ማን ነው? የሚፈልጋት ሁሉ ራሱን አያደክምም። ወደ እርሷ ሄደው በትኩሳቷ ወራት ያገኟታል። \v 25 እግርሽን ባዶ ከመሆን፣ ጉሮሮሽንም ከውኃ ጥም ከልክዪ! አንቺ ግን 'ተስፋ-ቢስ ነው! አይሆንም፣ እንግዶችን ወድጄአለሁና እከተላቸዋለሁ!' አልሽ።

1
02/26.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 26 ሌባ ሲያዝ እንደሚያፍረው ሁሉ፣ እንዲሁ የእስራኤል ቤት፣ እነርሱ፣ ንጉሦቻቸው፣ አለቆቻቸው፣ ካህናቶቻቸውና ነብያቶቻቸውም ያፍራሉ። \v 27 ለዛፉ፣ 'አንተ አባቴ ነህ፣' ድንጋዮንም 'አንተ ወለድከኝ' ይላሉ። ፊታቸውንም ሳይሆን ጀርባቸውን ሰጡኝ። በመከራቸው ጊዜ ግን 'ተነሥና አድነን!' ይላሉ። \v 28 ለአንተ የሠራሃቸው አማልክትህ ወዴት ናቸው? ይሁዳ ሆይ፥ አማልክትህ እንደ ከተሞችህ ቊጥር እንዲሁ ናቸውና ይነሡ በመከራህም ጊዜ ያድኑህ!

1
02/29.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 29 ስለዚህ እኔ እንዳጠፋሁ አድርጋችሁ የምትከስሱኝ ለምንድር ነው? ሁላችሁ በእኔ ላይ ኃጢአት ሠርታችሁብኛል ይላል እግዚአብሔር። \v 30 ሕዝባችሁን በከንቱ ቀጥቼአቸዋለሁ፤ ተግሣጽን አልተቀበሉም፤ እንደሚሰብር አንበሳ ሰይፋችሁ ነቢያቶቻችሁን በልቶአል! \v 31 ከዚህ ትውልድ የሆናችሁ እናንተ! የእግዚአብሔር ቃል ለሆነው ለቃሌ ትኩረት ስጡ! በውኑ ለእስራኤል ምድረ በዳ፣ ወይስ የጥልቅ ጨለማ ምድር ሆንሁባትን? ሕዝቤስ ስለ ምን 'እኛ እንቅበዝበዝ፣ ከእንግዲህ ወዲህ ወደ አንተ አንመለስም' ይላል?

1
02/32.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 32 ደናግሏ ጌጥዋን፣ ወይስ ሙሽራ ዝርግፍ ጌጥዋን ትረሳለችን? ሕዝቤ ግን ለማይቈጠሩ ቀናት ረስቶኛል። \v 33 ፍቅርን ለመሻት መንገድሽን እንዴት በደህና ታቀኛለሽ። እንደውም መንገድሽን ለክፉዎች ሴቶች እንኳ አስተምረሻል። \v 34 የንፁሐን ሕይወት የሆነው ደም፣ የድሆችም ደም በልብሶችሽ ላይ ተገኝቷል። እነዚህ ሰዎች በስርቆሽ ተግባር የተያዙ አልነበሩም።

1
02/35.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 35 ይልቊን፣ ይህ ሁሉ ሆኖ ሳለ፣ 'ወቀሳ የለብኝም፤ በእውነት የእግዚአብሔር ቊጣ ከእኔ ተመልሶአል' አልሽ። ነገር ግን ተመልከቺ! 'ኃጢአት አልሠራሁም' ብለሻልና ይፈረድብሻል። \v 36 መንገድሽን ትለዋውጪ ዘንድ ነገሩን ለምን ታቀልያለሽ? አሦር እንዳሳፈረሽ ግብጽ ያሳፍርሻል። \v 37 እግዚአብሔር የታመንሽባቸውን ጥሎአልና፥ በእነርሱም አይከናወንልሽምና እጅሽን በራስሽ ላይ አድርገሽ ከዚያ ደግሞ ትወጫለሽ።

1
03/01.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 1 በሰው ዘንድ፣ 'ሰው ሚስቱን በፍቺ ቢያባርራት፣ ከእርሱም ሄዳ የሌላ ሰው ሚስት ትሆናለች። በድጋሚ ወደ እርሷ ሊመለስ ይገባዋልን? እርሷ ፈጽሞ የረከሰች አይደለችምን?' ይባላል። ያቺ ሴት ማለት ይህች ምድር ናት! አንቺ እንደ ሴተኛ አዳሪ ከብዙ ውሽሞች ጋር አመንዝረሻል፣ ወደ እኔም ትመለሻለሽን? ይላል እግዚአብሔር። \v 2 ዓይንሽን ወደ ተራቆቱት ኮረብቶች አንሺና ተመልከቺ! ያልተነወርሽበት ስፍራ ወዴት አለ? ዘላን በምድረ በዳ እንደሚቀመጠው፣ አንቺ በመንገድ ላይ ተቀምጠሽ አፍቃሪዎችሽን ትጠብቂያቸው ነበር። በዘማዊነትሽና በኃጢአትሽ ምድሪቱን አረከስሽ።

1
03/03.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 3 ስለዚህ የጸደይ ዝናብ ተከለከለ፣ የኋለኛውም ዝናብ አልመጣም። ነገር ግን እንደ ዘማዊት ሴት ፊት፣ ፊትሽ የእብሪተኛ ነበር። ልታፍሪም እንቢ ብለሻል። \v 4 ከእንግዲህ ወዲህ 'አባቴ! የወጣትነቴ የቅርብ ወዳጅ ነህ።' ብለሽ ወደ እኔ አልጮኽሽልኝምን? \v 5 እስከ ለዘላለም ትቆጣለህን? ቊጣህንስ እስከ ፍጻሜ ድረስ ትጠብቀዋለህን?' ብለሽ ተናገርሽ። ተመልከቺ! ክፋትን እንደምትፈጽሚ ተናገርሽ፣ አደረግሸውም። ስለዚህ ማድረግሽን ቀጥይ!"

1
03/06.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 6 እግዚአብሔርም በንጉሡ በኢዮስያስ ዘመን እንዲህ አለኝ "እስራኤል እኔን መክዳቷን ታያለህ? ከፍ ወዳለው ተራራ ሁሉ፣ ወደለመለመ ዛፍም ሁሉ በታች ሄደች፣ በዚያም እንደ ዘማዊት ሴት ሆነች። \v 7 'ይህንም ሁሉ ካደረገች በኋላ፣ ወደ እኔ ትመለሳለች' ብዬ ነበር፤ ነገር ግን አልተመለሰችም። ከዚያም እምነት የለሿ እኅቷ ይሁዳ እርሷ ያደረገችውን አየች።

1
03/08.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 8 ስለዚህ፣ ለእነዚህ ምክንያቶች ሁሉ ማመንዘሯን አየሁ። ከዳተኛይቱ እስራኤል! ፈትቼያት አባርሬያታለሁ፣ ደግሞም የፍችዋንም ወረቀት ሰጥቻታለሁ። አታላይ እኅትዋ ይሁዳ ግን አልፈራችም፣ እርስዋም ደግሞ ሄዳ ዝሙትን ፈጸመች። \v 9 በዝሙትዋ ምድሪቱ መርከሷ ምንም አልመሰላትም፣ ስለዚህ ከድንጋይና ከግንድ ጣዖታትን አደረጉ። \v 10 ከዚያም ይህ ሁሉ ከሆነ በኋላ፣ እምነት-የለሿ ይሁዳ በውሸት እንጂ በፍጹም ልብዋ ወደ እኔ አልተመለሰችም!"-ይላል እግዚአብሔር።

1
03/11.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 11 ከዚያም እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፣ "ከእምነት-የለሿ ይሁዳ ይልቅ እምነት-የለሿ እስራኤል ጸደቀች! \v 12 ሂድና ይህን ቃል ለሰሜን ተናገር። 'እምነት የለሿ እስራኤል ሆይ፥ ተመለሽ! ይላል እግዚአብሔር፤ ለሁልጊዜ አልቈጣብሽምና። እኔ ታማኝ ስለሆንኩ - ለዘላለም እንደተቆጣሁ አልቆይም ይላል እግዚአብሔር።

1
03/13.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 13 በአምላክሽ በእግዚአብሔር ላይ እንዳመፅሽ፥ መንገድሽንም ከለመለመ ዛፍ ሁሉ በታች ለእንግዶች እንደ ዘረጋሽ፥ ቃሌንም እንዳልሰማሽ ኃጢአትሽን ዕወቂ ይላል እግዚአብሔር። \v 14 አግብቻችኋለሁና እምነት-የለሽ የሆናችሁት ሕዝቦች፣ ተመለሱ! ይላል እግዚአብሔር፤ አንዱንም ከአንዲት ከተማ ሁለቱንም ከአንድ ወገን እወስዳችኋለሁ! ወደ ጽዮንም አመጣችኋለሁ! \v 15 እንደ ልቤም የሆኑ እረኞችን እሰጣችኋለሁ፣ እነርሱም በዕውቀትና በማስተዋልም ይጠብቁአችኋል።

1
03/16.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 16 በእነዚያ ቀናት ትበዛላችሁ፣ በምድሪቱም ላይ ታፈራላችሁ ይላል እግዚአብሔር። "የእግዚአብሔር የቃል ኪዳኑ ታቦት!" ብለው ከእንግዲህ ወዲህ አይናገሩም። ከእንግዲህ አያስቡትምና፣ ወይም አያስተውሉትምና ይህ ጉዳይ ከእንግዲህ በልባቸው አይመጣም። ከእንግዲህ ወዲህም ይህ ንግግር አይኖርም።'

1
03/17.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 17 በዚያም ዘመን ስለ ኢየሩሳሌም 'ይህች የእግዚአብሔር ዙፋን ናት' ብለው ይናገራሉ፣ ደግሞም ሌሎች አሕዛብ ሁሉ በእግዚአብሔር ስም ኢየሩሳሌም ላይ ይሰበሰባሉ። ከእንግዲህም ወዲህ በእልከኛ ልባቸው አይሄዱም። \v 18 በእነዚያም ቀናት፣ የይሁዳ ቤት ከእስራኤል ቤት ጋር ይሄዳል። በአንድም ሆነው ከሰሜን ምድር ርስት አድርጌ ለአባቶቻቸው ወደ ሰጠኋት ምድር ይመጣሉ።

1
03/19.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 19 እኔ ግን 'እንደ ወንድ ልጄ ላከብርሽና በሌሎች አሕዛብ ካለው ይልቅ የበለጠ ውብ የሆነውን አስደሳቹን ምድር ልሰጥሽ እንዴት ፈለግሁ!' ብዬ ነበር። "አባቴ" ብለሽ ትጠሪኛለሽ። እኔንም ከመከተል አትመለሽም' ብዬ ነበር። \v 20 ነገር ግን ለባሏ ታማኝ እንዳልሆነች ሴት፣ እንዲሁ የእስራኤል ቤት የሆናችሁት ከዳችሁኝ ይላል እግዚአብሔር።

1
03/21.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 21 "የእስራኤል ልጆች መንገዳቸውን ቀይረዋልና፣ አምላካቸውንም እግዚአብሔርን ረስተውኛልና በወና ኮረብቶች ላይ የልመናቸውና ልቅሶአቸው ድምፅ ተሰማ። \v 22 ከዳተኞች ሕዝቦች ሆይ ተመለሱ! ከዳተኛነታችሁንም እፈውሳለሁ!" እነሆ! አንተ አምላካችን እግዚአብሔር ነህና ወደ አንተ እንመጣለን።

1
03/23.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 23 የኮረብቶችና የብዙ ተራሮች ሐሰት ብቻ መጥቷል። በእርግጥም የእስራኤል መዳን በአምላካችን በእግዚአብሔር ነው። \v 24 ይሁን እንጂ አሳፋሪ ጣዖታት ለበጎቻቸውና ላሞቻቸው፣ ለወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸው አባቶቻችን የሠሩትን በልተውባቸዋል። \v 25 በእፍረት እንጋደም። በአምላካችን እግዚአብሔር ላይ ኃጢአት ሠርተናልና እፍረታችን ይሸፍነን። ከትንሽነታችን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እኛና አባቶቻችን በአምላካችን በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአት ሠርተናልና፣ የአምላካችንንም የእግዚአብሔርን ቃል አልሰማንምና!"

1
04/01.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 1 እስራኤል ሆይ፣ ብትመለሺ፣ የምትመለሺው ወደ እኔ ይሁን፣ ይላል እግዚአብሔር፤ ከፊቴ ርኩሰትሽን ብታስወግጂ፣ በድጋሚም ከእኔ ባትርቂ \v 2 'ሕያው እግዚአብሔርን!' ብለሽ በእውነትና በፍትሕ፣ በጽድቅም ብትምይ፥ አሕዛብ በረከቴን ይጠይቃሉ፣ እኔንም ያመሰግኑኛል። \v 3 ለይሁዳና ለኢየሩሳሌም ሰዎች እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ 'ጥጋቱን እርሻ እረሱ፣ በእሾህም ላይ አትዝሩ።

1
04/04.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 4 እናንተም የይሁዳ ሰዎች፣ የኢየሩሳሌምም ነዋሪዎች፣ ስለ ሥራችሁ ክፋት ቊጣዬ እንደ እሳት እንዳይወጣ የሚያጠፋውም ሳይኖር እንዳያቃጥል፥ ለእግዚአብሔር ተገረዙ፥ የልባችሁንም ሸለፈት አስወግዱ። \v 5 ይሁዳ ውስጥ ተናገሩ፣ በኢየሩሳሌምም ላይ አውሩ። "በአገሪቱ ላይ መለከት ንፉ" በሉ፤ ጮኻችሁም "ሁላችሁ ተሰብሰቡ። ወደ ተመሸጉትም ከተሞች እንግባ" በሉ። \v 6 ከሰሜን ክፉ ነገርንና ጽኑ ጥፋትን አመጣለሁና ወደ ጽዮን ሰንደቅ ዓላማን አንሡ፤ ሽሹ፥ አትዘግዩ።

1
04/07.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 7 አንበሳ ከጥቅጥቅ ዱር እየወጣ ነው፣ አሕዛብንም የሚያጠፋ እየወጣ ነው። ምድርሽን ለማሸበር፣ ከተሞችሽም ሰው የሌለባቸው ፍርስራሾች ለማድረግ ከስፍራው ወጥቶአል። \v 8 ከዚህ የተነሣ፣ ራስሽን በማቅ ልብስ ሸፍኚ፣ ሙሾ አውጪ፣ አልቅሺም። የእግዚአብሔር ጽኑ ቊጣ ከእኛ ዘንድ አልተመለሰምና።

1
04/09.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 9 በዚያም ቀን፥ ይላል እግዚአብሔር፥ የንጉሡና የመኳንንቱ ልብ ይሞታል። ካህናቱም ይደነቃሉ ነቢያቱም ይደነግጣሉ። \v 10 እኔም "ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! ወዮ፥ 'ሰላም ይሆንላችኋል' በማለት ይህን ሕዝብና ኢየሩሳሌምን በእርግጥም ፈጽመህ አታልለሃል። ሆኖም 'ሰይፉ እስከ ነፍስ ድረስ ያጠቃል።"

1
04/11.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 11 በዚያ ጊዜ ለዚህ ሕዝብና ለኢየሩሳሌም፣"የሚያቃጥል ነፈሳስ በምድረበዳ ካሉት ወና ኮረብቶች ወደ ሕዝቤ ሴት ልጅ ይመጣል። እነርሱን አያበጥርም ወይም አያጠራም። \v 12 ከዚያም ይልቅ እጅግ ብርቱ የሆነ ነፋስ በትእዛዜ ይመጣል፣ ደግሞም እኔ ፍርዴን በእነርሱ ላይ እናገራለሁ።

1
04/13.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 13 ተመልከቱ እንደ ደመና ያጠቃል፣ ሠረገሎቹም እንደ ዐውሎ ነፋስ ናቸው። ፈረሶቹም ከንስር ይልቅ ፈጣኖች ናቸው። ጠፍተናልና ወዮልን! \v 14 ኢየሩሳሌም ሆይ፣ ትድኚ ዘንድ ልብሽን ከክፉ ነገር እጠቢ። እንዴት ኃጢአት እንደምትሠሪ ክፉ አሳብ የሚኖርብሽ እስከ መቼ ድረስ ነው? \v 15 የተናጋሪ ድምፅ ከዳን ይናገራል። የሚመጣውም ጥፋት ከኤፍሬምም ተራሮች ይሰማል።

1
04/16.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 16 አሕዛብ ይህንን እንዲያስቡ አድርጉ፦ ተመልከቱ፣ ወራሪዎች በይሁዳ ከተሞች ላይ የጦርነት ጩኸት ለመጮኽ ከሩቅ ምድር እየመጡ ነው ብላችሁ አውሩ። \v 17 በእኔ ላይ ዓመፀኛ ሆናለችና የለማ እርሻን ከብበው እንደሚጠብቊ ይሆናሉ ይላል እግዚአብሔር። \v 18 ባሕርይሽና ሥራሽ ይህን አድርጎብሻል። ይህ ቅጣትሽ ይሆናል። እንዴት አስጨናቂ ይሆናል! የገዛ ልብሽም ይመታል።

1
04/19.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 19 ልቤ! ልቤ! በልቤ ተጨንቄያለሁ። ልቤ በውስጤ ታውኮብኛል። የመለከትን ድምፅና የጦርነት ማንቂያን ሰምቻለሁና ዝም ልል አልችልም። \v 20 በጥፋት ላይ ጥፋት ተጠርቶአል፣ መላዋ ምድርም ተበዝብዛለች። በድንገትም ድንኳኔንና መጋረጃዬን አጠፉ።

1
04/21.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 21 መስፈርቱን የምመለከተው እስከመቼ ነው? የመለከቱንስ ድምፅ እሰማ ይሆን? \v 22 ሕዝቤ ተሞኝተዋልና አላወቁኝም። ሰነፍ ሕዝብ ናቸው፣ ማስተዋልም የላቸውም። ክፉ ነገርን ለማድረግ ብልሃተኞች ናቸው፣ በጎ ነገርን ማድረግ ግን አያውቁም።

1
04/23.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 23 ምድሪቱን አየሁ፣ እነሆም፥ ባዶ ነበረች አንዳችም አልነበረባትም፤ ለሰማያትም ብርሃንም አልነበረባቸውም። \v 24 ተራሮችን አየሁ። እነሆም፣ ይንቀጠቀጡ ነበር፣ ኮረብቶችም ሁሉ ተናወጡ። \v 25 አየሁ። እነሆ፣ ሰው አልነበረም፣ የሰማይም ወፎች ሁሉ ሸሽተው ነበር። \v 26 ተመለከትሁ። እነሆ፣ ፍሬያማ እርሻ ምድረ በዳ ሆነች፣ ከተሞችም ሁሉ ከእግዚአብሔር ፊት ከጽኑ ቊጣው የተነሣ ፈርሰው ነበር።

1
04/27.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 27 እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል "ምድር ሁሉ ትጠፋለች፣ ነገር ግን ፈጽሜ አላጠፋቸውም። \v 28 ስለዚህ ምድር ታለቅሳለች፣ ከላይ ያለው ሰማይ ይጠጨልማል። ተናግሬአለሁና፥ አስቤአለሁም፤ አልጸጸትም ከመፈጸምም አልመለስም። \v 29 ከፈረሰኞችና ከቀስተኞች ጫጫታ የተነሣ እያንዳንዱ ከተማ ሁሉ ይሸሻሉ፤ ወደ ጫካም ይገባሉ። እያንዳንዱ ከተማ በቋጥኝ ላይም ይወጣሉ። ከተሞቹ ይተዋሉ፣ የሚኖርባቸው ሰው አይኖርምና።

1
04/30.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 30 አንቺም ባድማ ሆንሽ፥ ምን ታደርጊአለሽ? ቀይ በለበስሽ ጊዜ፥ በወርቅ አንባርም አጌጥሽ፣ ዓይንሽንም ተኳልሽ፣ የሚመኙሽ ወንዶች ገፉሽ። ይልቊን፣ ነፍስሽን ይሹአታል። \v 31 ስለዚህ የምጥ፣ የበኩር ልጅ እንደሚወለድበት ያለ የጭንቅ ድምጽ፣ የጽዮን ሴት ልጅን ድምጽ ሰምቻለሁ። ለመተንፈስ ትታገላለች። እጆቿንም ትዘረጋለች፣ ከገዳዮቹ የተነሣ ነፍሴ ዝላለችና 'ወዮልኝ!' አለች።

1
05/01.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 1 በኢየሩሳሌም መንገድ እየተመላለሳችሁ ሩጡ፤ በአደባባዮችዋም ፈልጉ። ከዚያም ተመልከቱ፣ ስለዚህም አስቡ፦ ፍትሕን የሚያደርገውን በታማኝነትም ለማድረግ የሚሞክረውንም ሰው ታገኙ እንደሆነ፣ ይቅር እላታለሁ። \v 2 እነርሱም 'ሕያው እግዚአብሔርን!' ቢሉ የሚምሉት በሐሰት ነው። \v 3 እግዚአብሔር ሆይ፣ ዓይንህ ታማኝነትን የምትመለከት አይደለችምን? አንተ ቀሥፈሃቸዋል፣ ነገር ግን አላመማቸውም። ሙሉ ለሙሉ አሸንፈሃቸዋል፣ ነገር ግን ተግሣጽን እንቢ አሉ። ፊታቸውን ከድንጋይ ይልቅ አጠንክረዋል፤ ይመለሱ ዘንድ እንቢ አሉ።

1
05/04.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 4 ስለዚህ እኔም "እነዚህ ድሆች ብቻ የሆኑ ሕዝቦች ናቸው። የእግዚአብሔርን መንገድና የአምላካቸውን ሕግ አላወቁምና እነዚህ ሰነፎች ናቸው፤ \v 5 ወደ ጠቃሚዎቹ ሕዝቦች እሄዳለሁ የእግዚአብሔርን መልእክት እናገራቸዋለሁ፤ የእግዚአብሔርን መንገንድና የአምላካቸውን ሕግ ያውቃሉና። ነገር ግን እነርሱ በሙሉ ቀንበሩን በአንድነት ሰብረዋል፣ ለእግዚአብሔር ያሰራቸውንም ሰንሰለቶች ቈርጠዋል። \v 6 ስለዚህ ኃጢአታቸው በዝቶአልና፣ የክዳታቸውም ብዛት አይቆጠርምና አንበሳ ከዱር ወጥቶ ይሰብራቸዋል፣ የበረሀም ተኵላ ያጠፋቸዋል፣ ነብርም በከተሞቻቸው ላይ ይተጋል፣ ከዚያም የሚወጣ ሁሉ ይነጠቃል።

1
05/07.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 7 እነዚህን ሰዎች ይቅር የምላቸው ለምንድነው? ልጆችሽ ትተውኛል አማልክትም ባልሆኑትም ምለዋል። ሞልቼ መገብኳቸው፣ እነርሱ ግን አመነዘሩ የምንዝርና ቤትን ምልክቶችንም ወሰዱ። \v 8 በትኩሳት እንዳሉ ፈረሶች ሆኑ፤ ወዳጅነት ፈልገው ተንከላወሱ። እያንዳንዱ ሰው ወደባልንጀሮቻቸው ሚስቶች አሽካኩ። \v 9 ስለዚህ ልቀጣ አይገባኝምን? ይላል እግዚአብሔር፤ ነፍሴስ እንደዚህ ባለ ሕዝብ ላይ አትበቀልምን?

1
05/10.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 10 ወደ ወይን ከፍታዋ ወጥታችሁ አፍርሱ። ነገር ግን ፈጽማችሁ አታጥፏቸው። ወይኖቻቸውን ቊረጡ፣ እነዚህ ወይኖች ከእግዚአብሔር አልመጡምና። \v 11 የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ቤት በእኔ ላይ ፈጽሞ ከድተውኛልና ይላል እግዚአብሔር። \v 12 እነርሱም ከድተውኛል። 'እርሱ እውነተኛ አይደለም። ክፉ ነገርም አይመጣብንም፣ ሰይፍንና ራብንም አናይም' አሉ። \v 13 ነብያትም የነፋስን ያህል ጥቅም የለሽ ሆነዋል የእግዚአብሔርንም ቃል ለእኛ የሚነግረን የለም። ዛቻቸው በራሳቸው ላይ ይምጣባቸው።

1
05/14.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 14 ስለዚህም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል "በዚህ ቃል ተናግራችኋልና ተመልከት፣ በአፍህ ውስጥ ቃሌን አኖራለሁ። እንደ እሳት ይሆናል፣ ይህም ሕዝብ እንደ እንጨት ይሆናል! እሳቱም ይበላቸዋል። \v 15 ተመልከቱ! የእስራኤል ቤት ሆይ፣ ሕዝብን ከሩቅ አመጣባችኋለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር፤ ኃያል ጥንታዊ ሕዝብ ነው! ቋንቋቸውንም የማታውቋቸው፣ የሚናገሩትንም የማታስተውሉት ሕዝብ ነው።

1
05/16.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 16 የፍላጻቸውም ሰገባ እንደ ተከፈተ መቃብር ነው። ሁሉም ኃያላን ናቸው። \v 17 መከሮቻችሁንና እንጀራችሁን ይበላሉ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁንም ይበሏቸዋል፤ በጎችንና ላሞቻችሁንም ይበላሉ፤ ወይናችሁንና በለሶቻችሁንም ይበላሉ። የምትታመኗቸውን የተመሸጉ ከተሞችን በሰይፍ ይደበድባሉ።

1
05/18.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 18 ነገር ግን በዚያ ዘመን እንኳን ይላል እግዚአብሔር፣ ፈጽሜ ላጠፋችሁ አላስብም። \v 19 እንዲህም ይሆናል፤ እናንተ እስራኤል እና ይሁዳ፣ 'አምላካችን እግዚአብሔር ይህን ነገር ሁሉ ስለምን አደረገብን?' ስትሉ፣ አንተ ኤርምያስ ያን ጊዜ፣ 'እግዚአብሔርን እንደተዋችሁ እና በምድራችሁም ሌሎችን አማልክት እንዳመለካችሁ፣ እንዲሁ ለእናንተ ባልሆነ አገር ለሌሎች ሰዎች በባርነት ትገዛላችሁ' ትላቸዋለህ።

1
05/20.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 20 ይህን ለያዕቆብ ቤት አውሩ፣ በይሁዳም ይሰማ። \v 21 ይህን ስሙ፣ እናንተ ሰነፎች! ጣዖታት ፈቃድ የላቸውምና፤ ዐይን አለባቸው፣ ነገር ግን ሊያዩ አይችሉም። ጆሮዎችም አሉባቸው፣ ነገር ግን አይሰሙም። \v 22 እኔን አትፈሩኝምን? በፊቴስ አትደነግጡምን? ይላል እግዚአብሔር፤ የአሸዋን ድንበር እንዳይተላለፈው በማይቋረጥ ትእዛዝ በባሕሩ ላይ አድርጌአለሁ። የባህሩ ነውጥ ቢጮኽም አያቋርጠውም።

1
05/23.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 23 ነገር ግን ይህ ሕዝብ ግን ዐመፀኛ ልብ አለው። በዐመፅ ሸፍቶ ሄዷል። \v 24 በልባቸውም፣ 'የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ በትክክለኛው ጊዜ የሚሰጠውን፣ ለመከርም የተመደቡትን ወራት የሚጠብቅልንን አምላካችንን እግዚአብሔርን እንፍራ አላሉም። \v 25 በደላችሁ እነዚህ እንዳይሆኑ አስቀርታለች። ኃጢአታችሁም መልካምን ነገር ወደ እናንተ እንዳይመጣ አስቆመ።

1
05/26.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 26 በሕዝቤ መካከል ክፉዎች ሰዎች ተገኝተዋል። አንድ ሰው ወፎችን ለመያዝ ሲያደባ እንደሚመለከቱ፣ ወጥመድን ይዘረጋሉ ሰዎችንም ያጠምዳሉ። \v 27 ዋሻ ወፎችን እንደሚሞላ፣ እንዲሁ ቤታቸው ሽንገላን ሞልታለች። እንዲሁም ተልቀዋል፣ ባለ ጠጎችም ሆነዋል። \v 28 ወፍረዋል፣ በደህንነታቸውም ያብረቀርቃሉ። ክፋታቸውንም ያለ ልክ አብዝተዋል። ለሰዎች፣ ወይም ለወላጅ አልባዎች ነገር አልተምዋገቱላቸውም። ለችግረኞች ፍትሕን ባያደርጉም እንኳን በልጽገዋል። \v 29 ስለእነዚህ ነገሮች አልቀጣምን? ይላል እግዚአብሔር፤ እንደዚህ ባለ ሕዝብ ላይ ለራሴ አልበቀልምን?

1
05/30.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 30 በምድር ላይ የምታስደንቅና የምታስደነግጥ ነገር ሆናለች፤ \v 31 ነቢያት በሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፣ ካህናትም በገዛ ኃይላቸው ይገዛሉ። ሕዝቤም እንዲህ ያለውን ነገር ይወድዳሉ፣ ነገር ግን በፍጻሜው ምን ይፈጠራል?

1
06/01.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 1 እናንተ የብንያም ሕዝቦች፣ ከኢየሩሳሌም በመሸሽ ደህንነትን አግኙ። በቴቁሔ መለከትን ንፉ። ታላቅ ጥፋት የሆነ ክፉ ነገር ከሰሜን እየመጣ ነውና በቤትሐካሬም ላይ ምልክትን አንሡ። \v 2 የተዋበችውና ሰልካካዋን የጽዮንን ልጅ እደመስሳለሁ። \v 3 እረኞችና መንጐቻቸው ወደ እርስዋ ይሄዳሉ፣ በዙሪያዋም ድንኳኖቻቸውን ይተክሉባታል፣ እያንዳንዱም እረኛ በገዛ እጁ መንጋውን ይጠብቃል።

1
06/04.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 4 ነገሥታት "ለአማልክቶቻችሁ እንድትዋጉ ራሳችሁን አስገዙ። ተነሡ፣ በቀጥርም እናጥቃ። ቀኑ እየመሸ መሆኑ፣ የማታውም ጥላ እየረዘመ መሆኑ እጅግ መጥፎ ነው። \v 5 ነገር ግን በሌሊትም እናጥቃ፣ አምባዎችዋንም እናፍርስ።

1
06/06.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 6 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ዛፎችዋን ቍረጡ፥ በኢየሩሳሌምም ላይ የከበባ አፈርን ደልድሉ፤ ይህች በግፍ የተሞላች ከተማ በመሆኗ ለማጥቃት ትክክለኛዋ ከተማ ነች። \v 7 ጕድጓድ ውኃ ማፍለቊን እንደሚቀጥል፣ እንዲሁ ይህች ከተማ ክፋትን ማፍለቋን ትቀጥላለች። ዐመጽና ሥርዓተቢስነት በእርስዋ ዘንድ ይሰማል። መከራና መቅሠፍትም ሳይቋረጥ በፊቴ አለ። \v 8 ኢየሩሳሌም ሆይ፣ ከአንቺ እንዳልለይ፣ አንቺንም ባድማና ወና እንዳላደርግሽ፣ ተግሣጽን ተቀበዪ።"

1
06/09.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 9 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ሰው ወይኑን እንደሚለቅም፣ እንዲሁ ከእስራኤል የቀሩትን በእርግጥ ይቃርሟቸዋል፤ በድጋሚ እጅህን ዘርግተህ ወይንን ከግንዱ እንደሚለቅም አድርግ። \v 10 ይሰሙኝስ ዘንድ ለማን እናገራለሁ፣ ለማንስ አስጠነቅቃለሁ? ተመልከቱ! ጆሮአቸው ያልተገረዘ ነው፤ በትኩረት ለመስማት አይችሉም! ተመልከቱ! የእግዚአብሔር ቃል ሊያቀናቸው መጥቶባቸዋል፣ ነገር ግን አይፈልጉትም።"

1
06/11.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 11 ነገር ግን በእግዚአብሔር ቍጣ ተሞልቻለሁ። በውስጤ ይዤ ልታገሠው ደክሜአለሁ። እንዲህ አለኝ፣ "በጎዳና ሕፃናት ላይ፣ እንዲሁም በወጣቶችም ስብስብ ላይ አፍስሰው። እያንዳንዱ ባል ከሚስቱ ጋር እድሜ ጠገቡ ሽማግሌም ከጎበዙ ጋር ይወሰዳልና። \v 12 ቤቶቻቸው እርሻዎቻቸውም ሚስቶቻቸውም በአንድነት ለሌሎች ይሆናሉ። በምድር የሚገኙ ነዋሪዎችን አጠቃለሁና ይላል እግዚአብሔር።

1
06/13.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 13 ከታናሻቸው ጀምሮ እስከ ታላቃቸው ድረስ እያንዳንዳቸው በኃቅ ላልሆነ ትርፍ ስስታሞች ናቸው። ከነቢዩም ጀምሮ እስከ ካህኑ ድረስ እያንዳንዳቸው በተንኰል ይመላለሳሉ። \v 14 የሕዝቤንም ስብራት የሚፈውሱት ግን በጥቂቱ ነው፣ ሰላም ሳይኖር 'ሰላም ሰላም!' ይላሉ። \v 15 ርኩስን ነገር ስለሠሩ አፍረዋልን? በጭራሽ አልፈሩም፣ ማንኛውንም እፍረት አላወቁም። ስለዚህ በምቀጣቸው ጊዜ ከሚወድቁ ጋር ይወድቃሉ። ይገለበጣሉ፣" ይላል እግዚአብሔር።

1
06/16.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 16 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "በመንገድ ማቋረጫ ላይ ቁሙና ተመልከቱ፣ የቀደመችውንም መንገድ ጠይቁ። 'መልካሚቱ መንገድ ወዴት ናት?' በሉና በእርስዋ ላይ ሄዳችሁ ለነፍሳችሁ ዕረፍትን አግኙ። ሕዝቡ ግን፣ 'አንሄድባትም' አሉ። \v 17 እኔም የመለከቱን ድምፅ እንዲያደምጡ ጠባቂ ጉበኞችን ሾምሁላችሁ። እነርሱ ግን፣ 'አናደምጥም' አሉ። \v 18 አሕዛብ ሆይ፥ አድምጡ! ተመልከቱ፣ በእነርሱ ላይ የሚደርስባቸውን ትመሰክራላችሁ። \v 19 ምድር ሆይ፣ ስሚ! ተመልከቺ፣ የአሳባቸው ፍሬ የሆነ ጥፋትን በዚህ ህዝብ ላይ ላመጣ ነው። ለቃሌ ወይም ለህጌ ምንም ትኩረት አልሰጡም፣ ነገር ግን ከዚያ ይልቅ አጣጣሉት።"

1
06/20.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 20 ከሳባ የሚቀርበው ዕጣን ለእኔ ምን ማለት ነው? ወይስ ከሩቅም አገር የሆነው ጣፋጭ ሽታ ምንድነው? የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁን፣ እንዲሁም መስዋዕቶቻችሁን አልቀበለውም። \v 21 ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል 'ተመልከቱ፣ በዚህ ሕዝብ ፊት ዕንቅፋቶችን አደርጋለሁ። አባቶችና ልጆች በአንድነት ይሰናከሉባቸዋል። ነዋሪዎችና ጎረቤቶቻቸው ይጠፋሉ። \v 22 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል 'ተመልከቱ፣ ሕዝብ ከሰሜን ምድር ይመጣል። ታላቅ ሕዝብም ከምድር ዳርቻ ይነሣል።

1
06/23.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 23 ቀስትንና ጦርን ያነሣሉ። ጨካኞች ናቸው፣ ምሕረትንም የላቸውም። ድምፃቸው እንደ ባሕር ጩኸት ነው፣ በጽዮን ሴት ልጅ ላይ እንደሚዋጉ በፈረሶችም ላይ ይጋልባሉ።" \v 24 ስለ እነርሱ ወሬውን ሰምተናል። እጃችን በጭንቀት ዝላለች። ምጥ ወላድን ሴት እንደሚይዛት ጭንቀት ይዞናል።

1
06/25.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 25 የጠላት ሰይፍና ሽብር ስለከበባችሁ ወደ ሜዳ አትውጡ፣ በመንገድም ላይ አትሂዱ። \v 26 የሕዝቤ ሴት ልጅ ሆይ፣ ማቅ ልበሺና ለብቸኛ ልጅ መቀበሪያ አፈር ውስጥ ተንከባለዪ። አጥፊው በድንገት ይመጣብናልና ለራስሽ መራራ የሆነ የቀብር ለቅሶን አድርጊ።

1
06/27.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 27 "ኤርምያስ፣ መንገዳቸውን እንድትመረምርና እንድትፈትን በሕዝቤ መካከል ብረትን እንደሚፈትን አድርጌሃለሁ። \v 28 እነርሱ ሁሉ ሌሎችን የሚወነጅሉ እጅግ ዐመፀኞች ናቸው። በብልሹነት የሚመላለሱ ናስና ብረት ናቸው። \v 29 ወናፍ በሚያቃጥላቸው እሳት አናፋ፣ እርሳሱም በእሳቱ ቀለጠ። ክፋት ስላልተወገደ፣ የማጥራቱ ሥራ በመካከላቸው ይቀጥላል። \v 30 እግዚአብሔር ጥሎአቸዋልና የተጣለ ብር ብለው ይጠሯቸዋል።"

1
07/01.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 1 ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣ ቃል ይህ ነው፣ \v 2 በእግዚአብሔር ቤት በራፍ ላይ ቁም! እንዲህ በል፣ 'ይሁዳ ሁሉ ሆይ፣ እግዚአብሔርን ልታመልኩ በእነዚህ በራፎች የምትገቡ ሆይ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ።

1
07/03.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 3 የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ መንገዳችሁንና ሥራችሁን መልካም አድርጉ፣በዚህም ስፍራ መኖር እንድትቀጥሉ አደርጋችኋለሁ። \v 4 ራሳችሁን አታላይ በሆኑ ቃሎች ላይ ታምናችሁ፣ "የእግዚአብሔር መቅደስ! የእግዚአብሔር መቅደስ! የእግዚአብሔር መቅደስ!" አትበሉ።

1
07/05.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 5 መንገዳችሁንና ሥራችሁን ፈጽማችሁ መልካም ብታደርጉ፤ በሰውና በጎረቤቱ መካከል ቅን ፍርድ ብትፈርዱ፤ \v 6 በምድሪቱ የሚቆየውን እንግዳ፣ ወላጅ አልባውን፣ ወይም መበለቲቱንም ባትበዘብዙ፣ በዚህም ስፍራ ንጹሕ ደምን ባታፈስሱ፣ ለገዛ ጉዳታችሁ እንዲሆንባችሁ ሌሎች አማልክትን ባትከተሉ፤ \v 7 ያን ጊዜ ከጥንቱ ጊዜ ጀምሮ እስከ ለዘላለም ለአባቶቻችሁ በሰጠኋቸው ምድር በዚህ ስፍራ አሳድራችኋለሁ።

1
07/08.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 8 እነሆ! በማይረዳችሁ የሐሰት ቃል እየታመናችሁ ናችሁ። \v 9 ትሰርቃላችሁ፣ ትገድላላችሁ፣ ታመነዝራላችሁ? ደግሞም በሐሰትም ትምላላችሁ፣ ለበኣልም ታጥናላችሁ፣ የማታውቋቸውንም ሌሎች አማልክት ትከተላላችሁ? \v 10 ከዚያም መጥታችሁ ስሜም በተጠራበት በዚህ ቤት በፊቴ ቆማችሁ፣ እነዚህን ሁሉ ጥፋቶች ማድረግ እንድትችሉ "ድነናል፣" አላችሁ። \v 11 ይህስ ስሜ የተጠራበት ቤት በዓይናችሁ ፊት የሌቦች ዋሻ ሆኖአልን? ነገር ግን፣ እነሆ፣ እኔ አይቻለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር።

1
07/12.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 12 'ስለዚህ በቀድሞ ዘመን ስሜን ከመጀመሪያ ወዳሳደርሁበት በሴሎ ወደ ነበረው ስፍራዬ ሂዱ፣ ከሕዝቤም ከእስራኤል ክፋት የተነሣ ያደረግሁበትን እዩ። \v 13 ስለዚህ አሁንም፣ ይህን ሥራችሁን ሁሉ ስላደረጋችሁ፣ በተደጋጋሚ ጊዜ ተናገርኳችሁ፣ እናንተ ግን አልሰማችሁም። በጠራኋችሁም ጊዜ፣ አልመለሳችሁም። \v 14 ስለዚህ፣ በሴሎ እንዳደረግሁ፣ እንዲሁ ስሜ በተጠራበት በምትታመኑበት ቤት፣ ለእናንተና ለአባቶቻችሁም በሰጠኋችሁ ስፍራ ላይ እንዲሁ አደርጋለሁ። \v 15 የኤፍሬምንም ዘር የሆኑትን ወንድሞቻችሁን ሁሉ እንደ ጣልሁ፣ እንዲሁ ከፊቴ እጥላችኋለሁ።

1
07/16.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 16 ደግሞም አንተ፣ ኤርምያስ አልሰማህምና ለዚህ ሕዝብ አትጸልይ፣ ስለ እነርሱም ልመናና ጸሎት አታድርግ፣ አትማልድላቸው። \v 17 እነርሱ በይሁዳ ከተሞች ውስጥና በኢየሩሳሌም ጎዳናዎች ላይ የሚያደርጉትን አታይምን? \v 18 ያስቈጡኝ ዘንድ፣ ለሰማይ ንግሥት እንጐቻ እንዲያደርጉ ለሌሎችም አማልክት የመጠጥ ቍርባን እንዲያፈስሱ፣ ልጆች እንጨት ይሰበስባሉ፣ አባቶችም እሳት ያነድዳሉ፣ ሴቶችም ዱቄት ያቦካሉ።

1
07/19.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 19 በእውነት እኔን ያስቈጣሉን? ይላል እግዚአብሔር፤ ለእነርሱስ እፍረት እንዲሆንባቸው የሚያስቆጡት ራሳቸውን አይደለምን? \v 20 እንግዲያው ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'ተመልከቱ፣ ቍጣዬና መዓቴ በዚህ ስፍራ ላይ ይፈስሳል፣ በሰውና በአውሬው ላይ፣ በዱር ዛፎችና በምድር ፍሬ ላይ ይፈስሳል። ይነድዳል፣ መቼም አይጠፋም።'

1
07/21.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 21 የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'ለመሥዋዕታችሁ የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁን ጨምሩ፣ ከዚያም ላይ ሥጋውን ጨምሩ። \v 22 አባቶቻችሁን ከግብጽ ምድር ባወጣኋቸው ቀን፣ የትኛውንም ነገር ከእነርሱ አልጠየቅሁም። ስለሚቃጠል መሥዋዕትና ስለ ሌላ መሥዋዕት አላዘዝኋቸውምም። \v 23 ይህንን ትእዛዝ ብቻ ሰጠኋቸው፣ "ቃሌን ስሙ፣ እኔም አምላክ እሆናችኋለሁ እናንተም ሕዝብ ትሆኑኛላችሁ። መልካምም ይሆንላችሁ ዘንድ ባዘዝኋችሁ መንገድ ሁሉ ሂዱ።"

1
07/24.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 24 ነገር ግን በክፉ ልባቸው አሳብና እልከኝነት ሄዱ ወደ ፊትም ሳይሆን ወደ ፊታቸው ሳይሆን ወደ ኋላቸው ሄዱ እንጂ አልሰሙም ጆሮአቸውንም አላዘነበሉም። \v 25 አባቶቻችሁ ከግብጽ ምድር ከወጡበት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ፣ አገልጋዮቼን፣ ነቢያትን ሁሉ ልኬባችሁ ነበር። እነርሱን ተግቼ ላክሁባችሁ። \v 26 ነገር ግን አልሰሙኝም። ምንም ትኩረት አልሰጡም። ይልቊን፣ አባቶቻቸውም ካደረጉት ይልቅ የባሰ አደረጉ።

1
07/27.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 27 እነዚህን ቃሎች ሁሉ ንገራቸው፣ ነገር ግን አይሰሙህም። እነዚህን ነገሮች አውጅላቸው፣ ነገር ግን አይመልሱልህም። \v 28 የአምላኩን የእግዚአብሔርን ቃል ያልሰማ፣ ተግሣጽንም ያልተቀበለ ሕዝብ ይህ ነው። እውነት ጠፍቶአል ከአፋቸውም ተቈርጦአል በላቸው።

1
07/29.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 29 ፀጕርሽን ቍረጪ፣ ተላጪው፣ ጣዪውም። በወናዎች ኮረብቶችም ላይ ሙሾን አውጪ። እግዚአብሔር በቍጣው ይህንን ትውልድ ጥሎአልና፣ ትቶታልምና ። \v 30 የይሁዳ ልጆች በፊቴ ክፉን ነገር ሠርተዋል፣ ይላል እግዚአብሔር፤ ያረክሱትም ዘንድ ስሜ በተጠራበት ቤት ርኵሰታቸውን አኑረዋል።

1
07/31.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 31 ከዚያም ቶፌት ውስጥ በቤን ሄኖም ሸለቆ መስገጃዎችን ገነቡ። እኔም ያላዘዝሁትንና ፈጽሞ በልቤ ያላሰብሁትን ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን በእሳት ያቃጥሉ ዘንድ ይህንን አድርገዋል። \v 32 ስለዚህ፣ ተመልከቱ፣ ቶፌት ወይም የቤን ሄኖም ሸለቆ ተብሎ ዳግመኛ አይጠራም። የእርድ ሸለቆ ይባላል፤ የሚተርፍ ስፍራ እስኪታጣ ድረስ በቶፌት በድኖችን ይቀብራሉ ይላል እግዚአብሔር።

1
07/33.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 33 የዚህም ሕዝብ ሬሳ ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት መብል ይሆናል፣ የሚያስፈራራቸውም አይኖርም። \v 34 ምድሪቱም ወና ትሆናለችና ከይሁዳ ከተሞችና ከኢየሩሳሌም ጎዳናዎች ላይ የእልልታን ድምፅና የደስታን ድምፅ፣ የወንድ ሙሽራን ድምፅና የሴት ሙሽራን ድምፅ አጠፋለሁ።

1
08/01.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 1 በዚያን ዘመን፥ የይሁዳን ነገሥታት አጥንትና የመኳንንቶቹን አጥንት፥ የካህናቱን አጥንትና የነቢያቱን አጥንት፥ የኢየሩሳሌምንም ሰዎች አጥንት ከመቃብራቸው ያወጣሉ ይላል እግዚአብሔር። \v 2 በተከተሉአቸው፣ ባገለገሏቸውና በፈለጉአቸው፣ ባመለኳቸውም በፀሐይና በጨረቃ በሰማይም ሠራዊት ሁሉ ፊት ይዘረጉአቸዋል። አጥንቶቻቸው አይሰባሰቡም ወይም በድጋሚ አይቀበሩም። በምድር ፊት ላይ እንደ ጕድፍ ይሆናሉ። \v 3 እኔም ባሳደድኋቸው ስፍራ ሁሉ የቀሩት፣ ከዚህ ክፉ ሕዝብ የተረፉት ቅሬታዎች ሁሉ፣ ከሕይወት ይልቅ ሞትን ይመርጣሉ ይላል የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር።

1
08/04.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 4 እንዲህም ትላቸዋለህ፣ 'እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የትኛውም የወደቀ ሰው አይነሣምን? የጠፋስ ለመመለስ አይሞክርምን? \v 5 ይህ የኢየሩሳሌም ሕዝብ ዘላቂ በሆነ አለመታመን ስለ ምን ወደ ኋላው ይመለሳል? ተንኰልን ይዞአል ንስሃ ለመግባትም እንቢ ብሎአል።

1
08/06.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 6 አደመጥሁ ሰማሁም፣ ትክክለኛ ነገር አልተናገሩም፤ ማንም ስለ ክፋቱ ንስሃ አልገባም፣ ማንም "ምን አድርጌአለሁ?" አላለም። ወደ ጦርነት እንደሚሮጥ ፈረስ ሁላቸውም በየመንገዳቸው ሄዱ። \v 7 ሽመላ በሰማይ ትክክለኛ ጊዜዋን አውቃለች፤ ዋኖስና ጨረባ ዋልያም ያውቃሉ። እነርሱ ወደ ሚሰደዱበት የሚሄዱት በትክክለኛ ጊዜ ነው፣ ሕዝቤ ግን የእግዚአብሔርን ፍርድ አላወቁም።

1
08/08.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 8 እናንተስ፣ "ጥበበኞች ነን! የእግዚአብሔርም ሕግ ከእኛ ጋር ነው" እንዴት ትላላችሁ? በእርግጥ ተመልከቱ! የአታላይ ጸሐፊ ብዕር ማታለልን አድርጎአል። \v 9 ጥበበኞች ያፍራሉ። ደንግጠውማል ተጠምደዋል። ተመልከቱ! የእግዚአብሔርን ቃል ጥለዋል፣ ስለዚህ ጥበባቸው ምን ጥቅም አለው? \v 10 ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ስስታሞች ናቸውና፣ ከነቢዩም ጀምሮ እስከ ካህኑ ድረስ ሁሉ ያታልላሉና፣ ስለዚህ ሚስቶቻቸውን ለሌሎች፥ እርሻቸውንም ለሚወርሱባቸው እሰጣለሁ።

1
08/11.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 11 ቀላል ነገር እንደሆነ በማድረግ የሕዝቤን ሴት ልጅ ስብራት በጥቂቱ ይፈውሳሉ። ሰላም ሳይሆን፣ "ሰላም፣ ሰላም" ይላሉ። \v 12 አስጸያፊ ነገርን ስለ ሠሩ አፍረዋልን? ምንም አላፈሩም። ትሕትናም አልነበራቸውም። ስለዚህ በሚቀጡ ጊዜ ቀድሞውኑ ከወደቊት ጋር ይወድቃሉ ይላል እግዚአብሔር። \v 13 ፈጽሜ አጠፋችኋለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር፤ በወይን ላይ ፍሬ፣ በበለስ ዛፍ ላይ በለስ አይሆንም። ቅጠልም ይረግፋልና የሰጠኋቸውም ያልፋልና።

1
08/14.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 14 ለምን ዝም ብለን እንቀመጣለን? በአንድነት ኑ፤ ወደ ተመሸጉ ከተሞች እንሂድ፣ በዚያም በሞት ዝምተኞች እንሆናለን። እግዚአብሔር ዝም ያሰኘናልና። ስለ በደልነው መርዝ አጠጥቶናል። \v 15 ሰላምን በተስፋ ተጠባበቅን፣ ነገር ግን መልካም ነገር አልተገኘም። የፈውስ ጊዜን በተስፋ ተጠባበቅን፣ ነገር ግን ሽብር እንደሆነ ተመልከቱ።

1
08/16.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 16 የፈረሰኞች ድምጽ ከዳን ተሰማ። ከአርበኞች ፈረሶች ማሽካካት የተነሣ ምድር ሁሉ ተንቀጠቀጠች። ምድሪቱንና በእርስዋም ያለውን ሁሉ፥ ከተማይቱንና የሚኖሩባትንም ሊበሉ ይመጣሉና። \v 17 ተመልከቱ፣ አስማት የማይከለክላቸውን እባቦችንና እፉኝቶችን እሰድድባችኋለሁ። እነርሱም ይነድፉአችኋል" ይላል እግዚአብሔር።

1
08/18.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 18 ኅዘኔ ፍጻሜ የለውም፣ ልቤም ታምሞአል። \v 19 ተመልከቱ! እግዚአብሔር በጽዮን የለምን? ወይስ ንጉሥዋ በእርስዋ ዘንድ የለምን? የሚል የሕዝቤ ሴት ልጅ ጩኸት ድምፅ ከሩቅ ምድር ተሰማ። በተቀረጹ ምስሎቻቸውና በባዕድ ከንቱ ጣዖታት ያስቈጡኝ ስለ ምንድር ነው?

1
08/20.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 20 መከሩ አልፎአል፣ በጋው አብቅቷል። እኛ ግን አልዳንነም። \v 21 በሕዝቤ ሴት ልጅ ስብራት እኔ ተሰብሬአለሁ። በደረሰባት ነገር በጭንቀት አለቅሳለሁ፤ ጠቁሬማለሁ። \v 22 በገለዓድ መድኃኒት የለምን? ወይስ በዚያ ፈዋሽ የለምን? የሕዝቤ ሴት ልጅ ፈውስ ስለ ምን አልሆነም?

1
09/01.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 1 ተወግተው ስለ ሞቱ ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ሰዎች ሌሊትና ቀን አለቅስ ዘንድ ራሴ ውኃ፣ ዓይኔም የእንባ ምንጭ በሆነልኝ! \v 2 ሁሉም አመንዝሮች፣ የከዳተኞች ጉባኤ በመሆናቸው ሕዝቤን እተዋቸው ዘንድ ከእነርሱም እለይ ዘንድ በምድረ በዳ የመንገደኞች ማደሪያን ማን በሰጠኝ! \v 3 "አታላይ ቀስታቸው በሆነው በምላሳቸው ሐሰት ተናገሩ፣ ነገር ግን በምድር ላይ በታማኝነት ግሩም አይደሉም። ከክፋት ወደ ክፋት ይሄዳሉ። እኔንም አላወቁምና፣" ይላል እግዚአብሔር።

1
09/04.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 4 እያንዳንዱ ወንድም ሁሉ ያታልላልና፣ እያንዳንዱ ጎረቤትም ሁሉ ሐሜተኛ ስለሆነ እናንተ ሁሉ ከጎረቤቶቻችሁ ተጠንቀቁ፣ በወንድሞቻችሁም አትታመኑ። \v 5 እያንዳንዱ ሰውም ሁሉ ጎረቤቱን ያታልላል በእውነትም አይናገርም። ምላሶቻቸው የማታለል ነገሮችን ያስተምራል። በደልንም በማድረግ ይደክማሉ። \v 6 በማታለል መካከል ትኖራላችሁ፣ ከሽንገላም የተነሣ እኔን ያውቁኝ ዘንድ እንቢ ብለዋል፣ ይላል እግዚአብሔር።

1
09/07.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 7 ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ተመልከቱ፣ እፈትናቸዋለሁ። እመረምራቸዋለሁ። ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ክፋት ከዚህ ሌላ የማደርገው ምንድር ነው? \v 8 ምላሳቸው የተሳለ ፍላጻ ነው፤ ያልታመኑ ነገሮችን ይናገራሉ። ከጎረቤቶቻቸው ጋር በአንደበታቸው በሰላም ይናገራሉ፣ በልባቸው ግን ያደቡበታል። \v 9 በውኑ ስለዚህ ነገር አልቀጣቸውምን? ይላል እግዚአብሔር፤ እንደዚህስ ባለ ሕዝብ ላይ አልበቀልምን?

1
09/10.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 10 ለተራሮች የልቅሶና የዋይታን ዝማሬ እዘምራለሁ፣ ለምድረ በዳ ማሰማርያዎችም የቀብር ዋይታን እዘምራለሁ። ማንም ሰው እንዳያልፍባቸው በእሳት ተቃጥለዋልና። ሰዎችም የየትኛውንም ከብት ድምፅ አይሰሙም። የሰማይ ወፎች ጀምሮ እስከ እንስሳ ድረስ ሁሉ ሸሽተው ሄደዋል። \v 11 ኢየሩሳሌምን የፍርስራሽ ክምር፣ የቀበሮም ማደሪያ አደርጋታለሁ። የይሁዳንም ከተሞች ሰው የማይኖርባት ወና አደርጋቸዋለሁ። \v 12 ይህን የሚያስተውል ጠቢብ ሰው ማን ነው? ለሌሎች እንዲነግር የእግዚአብሔር አፍ ምን ተናገረው? ምድሪቱስ ስለምን ጠፋች? ማንም እንደማያልፍባት እንደ ምድረ በዳስ ስለ ምን ተደመሰሰች?

1
09/13.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 13 እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፣ "በፊታቸው የሰጠኋቸውን ሕጌን ስለተዉ፣ ድምጼንም አልሰሙምና ወይም አልተጓዙበትምና። \v 14 አባቶቻቸው እንዳስተማሯቸው በልባቸውን ምኞት ተመላልሰዋልና፣ በኣሊምን ተከትለዋልና።

1
09/15.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 15 ስለዚህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል 'ተመልከቱ፣ ይህን ሕዝብ እሬትን አበላዋለሁ የተመረዘንም ውኃ አጠጣዋለሁ። \v 16 እነርሱና አባቶቻቸውም ባላወቁአቸው አሕዛብ መካከል እበትናቸዋለሁ፣ እስካጠፋቸውም ድረስ በበስተኋላቸው ሰይፍን እሰድድባቸዋለሁ።"

1
09/17.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 17 የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ይህንን አስቡ፦ የቀብር አስለቃሾችን ጥሩ፤ ይምጡ። ወደ ብልሃተኛ አልቃሾች ላኩ። \v 18 ይፍጠኑና ዓይኖቻችንም እንባ እንዲያፈስሱ የዓይናችንም ሽፋሽፍቶች ውኃን እንዲያፈልቁ የለቅሶ ዝማሬን ይዘምሩልን።

1
09/19.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 19 'እንዴት ተበዘበዝን። ቤቶቻችን ስለፈረሱ ምድሪቱንም ትተናልና እንዴት አፈርን!' የሚል የልቅሶ ድምፅ በጽዮን ተሰምቶአል። \v 20 ስለዚህ እናንተ ሴቶች ሆይ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፣ ከአፉ ለሚወጣው ቃል ትኩረት ስጡ። ከዚያም ለሴቶች ልጆቻችሁም የልቅሶውን ዝማሬ አስተምሩ፣ ለእያንዳንዷም የጎረቤታችሁ ሴት የቀብሩን ሙሾ አስተምሩ።

1
09/21.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 21 ሞት ወደ መስኮታችን መጥቷልና፤ ወደ ቤተ መንግሥቶቻችን ሄዷል። ሕፃናቱን ከውጪ፣ ወጣቶቹንም ከከተማይቱ አደባባይ ያጠፋል። \v 22 'የሰውም ሬሳ በሜዳ ላይ እንደ ጕድፍ፣ ከአጫጆች በኋላ እንደሚቀር ቃርሚያ ይወድቃል፣ ማንምም አይሰበስበውም።

1
09/23.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 23 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ጠቢብ በጥበቡ እንዲመካ አትፍቀዱ፣ ወይም ጦረኛ በኃይሉ አይመካ። ባለ ጠጋም በብልጥግናው እንዲመካ አትፍቀዱ። \v 24 ሰው በየትኛውም ነገር የሚመካ ከሆነ፣ በዚህ ይሁን፣ ማስተዋል ያለውና የሚያውቀኝ በመሆኑ። የኪዳን ታማኝነት፣ ፍትሕንና ጽድቅንም በምድር ላይ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር ነኝና። ደስ የሚያሰኙኝ እነዚህ ናቸውና፣ ይላል እግዚአብሔር።

1
09/25.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 25 ተመልከቱ፣ በሰውነታቸው ብቻ የተገረዙትን እቀጣለሁ። \v 26 ግብጽንና ይሁዳን፣ የአሞን ሕዝቦች የሆኑትን ኤዶምያስና ሞዓብንም፣ እንዲሁም በምድረ በዳም የተቀመጡትን ፀጉራቸውን የተላጩትን ሁሉ፣ ባለመገረዛቸው ምክንያት የምቀጣበት ዘመን እነሆ ይመጣል። እነዚህ ሁሉ ሕዝቦች ያልተገረዙ ናቸውና፣ ደግሞም የእስራኤል ልብ አልተገረዘምና" ይላል እግዚአብሔር።

Some files were not shown because too many files have changed in this diff Show More