am_jdg_text_ulb/20/12.txt

4 lines
785 B
Plaintext

12 የእስራኤልም ነገዶች ወደ ብንያም ነገድ ሁሉ እንዲህ ብለው ሰዎችን ላኩ፣ “በእናንተ መካከል የተደረገው ይህ ክፉ ነገር ምንድር ነው?
13 ስለዚህ እንድንገድላቸውና ይህንን ክፋት ከእስራኤል ሙሉ ለሙሉ ለማስወገድ በጊብዓ ውስጥ ያሉትን እነዚህን ክፉ ሰዎች አውጥታችሁ ስጡን፡፡” ነገር ግን ብንያማውያን የወንድሞቻቸውን የእስራኤልን ሕዝብ ቃል አልሰሙም፡፡
14 የዚያን ጊዜ የብንያም ሕዝብ ከእስራኤል ሕዝብ ጋር ለመዋጋት ዝግጅት ያደርጉ ዘንድ ከየከተማው ወጥተው ወደ ጊብዓ ተሰበሰቡ፡፡