\v 8 ገልዓድ የክፉ አድራጊዎች ከተማ ነው፥ በደም ዱካ ተሞልቷል። \v 9 የቀማኞች ቡድን የሚዘርፉትን አድብተው እንደሚጠባበቁ፥ ካህናቱም በሴኬም መንገድ ላይ ሰው ለመግደል በቡድን ተደራጅተዋል፤ አሳፋሪም ወንጀል ይፈጽማሉ።