am_gal_text_ulb/03/06.txt

1 line
599 B
Plaintext

\v 6 ልክ አብርሀም «እንዳመነና እምነቱ እንደ ፅድቅ እንደተቆጠረለት» \v 7 የሚያምኑ ሁሉ የአብርሀም ልጆች እንደሆኑ አስተውሉ። \v 8 ቅዱሳት መፅሀፍት እግዚአብሔር አህዛብን እንደሚያፀድቅ አስቀድመው አመልክተዋል። ወንጌል « አህዛብ ሁሉ በአንተ ይባረካሉ» ተብሎ በመጀመሪያ ለአብርሀም ተሰብኳል። \v 9 ስለዚህም የሚያምኑ እምነት ከነበረው ከአብርሀም ጋር የተባረኩ ናቸው።