am_exo_text_ulb/40/28.txt

1 line
571 B
Plaintext

\v 28 መጋረጃውን በመገናኛው ድንኳን መግቢያ ላይ ሰቀለ። \v 29 የሚቃጠለውን መሥዋዕት መሠዊያም በማደሪያው፣ በመገናኛው ድንኳን መግቢያ አስቀመጠ። በመሠዊያውም ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቍርባን እግዚአብሔር እንዳዘዘው አቀረበ። \v 30 የመታጠቢያ ሳሕኑን በመገናኛው ድንኳንና በመሠውያው መካከል አኖረው፤ የመታጠቢያ ውሀም በውስጡ አደረገ።