am_2ki_text_ulb/05/15.txt

1 line
761 B
Plaintext

\v 15 ንዕማንና አጃቢዎቹ ወደ እግዚአብሔር ሰው ተመልሰው መጥተው በፊቱ ቆሙ፡፡ ንዕማንም እንዲህ አለ፡- ‹‹ከእስራኤል አምላክ በቀር በምድር ላይ ሌላ አምላክ እንደሌለ እነሆ አሁን ዐወቅሁ፡፡ ስለዚህም ከአገልጋይ ይህን ስጦታ እባክህ ተቀበለኝ›› አለው፡፡ \v 16 ኤልሳዕ ግን ‹‹በፊቱ ቆሜ በማገለግለው በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ፤ ምንም ስጦታ አልቀበልህም›› ሲል መለሰለት፡፡ ንዕማንም ስጦታውን እንዲቀበል አጥብቆ ቢለምነውም ኤልሳዕ ሊቀበለው አልፈቀደም፡፡