am_2ki_text_ulb/19/08.txt

1 line
554 B
Plaintext

\v 8 ከዚያ የአሦር የጦር አዛዥ፣ የአሦር ንጉሥ ከሰፈሩ ከለኪሶ ተነሥቶ ልብናን ሊያጠቃ እንደ ሄደ በመስማቱ እርሱም ወደ ለኪሶ ሄደ፡፡ \v 9 በኢትየጵያ ንጉሥ በቲርሃቅ የሚመራ የግብጽ ሠራዊት እነርሱን ለመውጋት በመገሥገሥ ላይ መሆኑን ሰናክሬም ሰማ፤ ወዲያውኑ የአሦር ንጉሠ ነገሥት ወደ ሕዝቅያስ እንዲህ የሚል ደብዳቤ በመልእክተኞች እጅ ላከ፡-