am_2ki_text_ulb/13/17.txt

1 line
1.1 KiB
Plaintext
Raw Blame History

This file contains ambiguous Unicode characters

This file contains Unicode characters that might be confused with other characters. If you think that this is intentional, you can safely ignore this warning. Use the Escape button to reveal them.

\v 17 ኤልሳዕ ‹‹የምሥራቁን መስኮት ክፈት›› አለ፤ ንጉሡም ከፈተው፤ ኤልሳዕም ‹‹ፍላጻውን አስፈንጥር! አለው፤ ንጉሡም ፍላጻውን እንዳስፈነጠረ ወዲያውኑ ኤልሳዕ፣ ‹‹ፍላጻ ነህ፤ በአንተም አማካይነት እግዚአብሔር ሶርያውያንን ድል ያደርጋል፤ ሶርያውያንን ድል እስክትነሣቸው ድረስ በአፌቅ ከተማ ትወጋቸዋለህ፡፡›› \v 18 ከዚህም በኋላ ኤልሳዕ ንጉሡን ‹‹ሌሎቹንም ፍላጻዎች አንሥተህ በእነርሱ ምድርን ምታ! አለው፡፡ ንጉሡም ምድርን ሦስት ጊዜ መትቶ አቆመ፡፡ \v 19 ይህም ኤልሳዕን አስቆጣው፤ ስለዚህም ንጉሡን ‹‹አምስት ወይም ስድስት ጊዜ መተህ ቢሆን ኖሮ በሶርያውያን ላይ ፍጹም ድልን ትቀዳጅ ነበር፤ አሁን ግን ሦስት ጊዜ ብቻ ድል ትነሣቸዋለህ›› አለው፡፡