Tue Jun 26 2018 12:22:22 GMT+0300 (E. Africa Standard Time)

This commit is contained in:
tsDesktop 2018-06-26 12:22:22 +03:00
parent 945372460b
commit 9c298f2b08
7 changed files with 12 additions and 0 deletions

1
16/01.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\c 16 \v 1 የሮሜልዩ ልጅ ፋቁሔ በእስራኤል በነገሠ በዐሥራ ሰባተኛው ዓመት የኢዮአታም ልጅ አካዝ የይሁዳ ንጉሥ ሆነ፡፡ \v 2 አካዝም በሚነግሠበት ጊዜ ዕድሜው ሃያ ዓመት ነበር፡፡ እርሱም በኢየሩሳሌም ዐሥራ ስድስት ዓመት ገዛ፡፡ እርሱም የቀድሞ አባቱን የንጉሥ ዳዊትን መልካም አርአያነት አልተከተለም፡፡ በአምላኩም በእግዚአብሔር ፊት ደስ የማያሰኝ ሥራ ሠራ፡፡

1
16/03.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 3 ይልቁንም የእስራኤልን ነገሥታት መጥፎ አርአያነት ተከተለ፡፡ የራሱን ልጅ እንኳ ሳይቀር ለጣዖታት የሚቃጠል መስዋዕት አድርጎ አቀረበ፤ ይህንንም ድርጊት የእስራኤል ሕዝብ ወደ ተስፋይቱ ምድር ከመግባቱ በፊት እግዚአብሔር ከእስራኤል ምድር ያስወገዳቸውን አሕዛብ ይሠሩት የነበረውን አስጸያፊ ድርጊት በመከተል ነበር፡፡ \v 4 አካዝ በየኮረብቶቹ ላይ በተሠሩት የአሕዛብ ማምለኪያ ስፍራዎችና በእያንዳንዱም ዛፍ ሥር መሥዋዕት በማቅረብ ዕጣን አጠነ፡፡

1
16/05.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 5 የሶርያ ንጉሥ ረአሶንና የእስራኤል ንጉሥ ፋቁሔ በኢየሩሳሌም ላይ አደጋ ለመጣል መጡ፤ ከበቧትም፡፡ ነገር ግን አካዝን ድል ሊያደርጉት አልቻሉም፡፡ \v 6 በዚያን ጊዜ የሶርያ ንጉሥ ረአሶን የኤላትን ከተማ አስመልሶ በቁጥጥሩ ሥር በማድረግ በዚያ የነበሩትን አይሁድ አስወጣ፡፡ ከዚያም በኤላት የሰፈሩት ኤዶማውያን እስከ አሁንም በዚያ ይኖራሉ፡፡

1
16/07.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 7 ስለዚህም ንጉሥ አካዝ ወደ አሦር ንጉሠ ነገሥት ወደ ቴልጌልቴልፌልሶር ‹‹እኔ ለአንተ ታማኝ አገልጋይህ ነኝ፤ አደጋ ከጣሉብኝ ከሶርያና ከእስራኤል ነገሥታት እጅ መጥተህ እኔን አድነኝ›› በማለት መልእክተኞችን ላከ፡፡ \v 8 አካዝም በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስና በቤተ መንግሥቱ ዕቃ ግምጃ ቤት የተገኘውን ብርና ወርቅ ሰብስቦ ለዚሁ ለአሦር ንጉሥ ገጸ በረከት በማድረግ ላከለት፡፡ \v 9 ከዚያም የአሦር ንጉሥ ቴልጌልቴልፌልሶር የአካዝን ጥያቄ በመቀበል ዘምቶ ደማስቆን በቁጥጥሩ ሥር አደረገ፡፡ ንጉሥ ረአሶንንም ገደለ፤ ሕዝቡንም ማርኮ ቂር ተብላ ወደምትጠራው ስፍራ ወሰደው፡፡

1
16/10.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 10 ንጉሥ አካዝም ከንጉሠ ነገሥት ቴልጌልቴልፌልሶር ጋር ለመገናኘት ወደ ደማስቆ ሄደ፡፡ በደማስቆም አንድ መሠዊያ አየ፡፡ ያንንም መሠዊያ በተመሳሳይ ሁኔታ መሥራት የሚያስችለውን ቅርጽ አዘጋጅቶ ለካህኑ ለኦሪያ ላከለት፡፡ \v 11 ስለዚህ ኦሪያ ንጉሥ አካዝ ከደማስቆ በላከለት ንድፍ መሠረት መሠዊያ ሠራ፡፡ \v 12 ንጉሡም ከደማስቆ በተመለሰ ጊዜ መሠዊያውን ተመለከተ፤ ወደ መሠዊያው ቀርቦም መሥዋዕት አቀረበ፡፡

1
16/13.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 13 በመሠዊያውም ላይ የሚቃጠል የእንስሶች መሥዋዕትና የእህል መባ አቀረበ፡፡ የመባውን ወይን ጠጅና የኅብረት መሥዋዕት ደም አፈሰሰበት፡፡ \v 14 ከነሐስ ተሠርቶ ለእግዚአብሔር የተለየውም መሠዊያ በዚያ አዲስ መሠዊያ፣ በቤተ መቅደሱ መካከል ነበር፤ ያንንም መሠዊያ አስነሥቶ እርሱ ባሠራው በአዲሱ መሠዊያ በስተሰሜን በኩል አኖረው፡፡

View File

@ -240,6 +240,12 @@
"15-32",
"15-34",
"16-title",
"16-01",
"16-03",
"16-05",
"16-07",
"16-10",
"16-13",
"17-title",
"18-title",
"19-title",