Tue Jun 26 2018 11:36:22 GMT+0300 (E. Africa Standard Time)

This commit is contained in:
tsDesktop 2018-06-26 11:36:22 +03:00
parent 323a88e181
commit 28f98bd90f
7 changed files with 12 additions and 0 deletions

1
06/12.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 12 ከእነርሱም አንዱ ‹‹ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፣ ከእኛ መካከል ይህን የሚያደርግ ማንም የለም፤ በመኝታ ክፍልህ እንኳ ሆነህ የምትናገረውን ሁሉ ሳይቀር ለእስራኤል ንጉሥ ምሥጢሩን የሚገልጥለት ኤልሳዕ የተባለው ነቢይ ነው›› ሲል መለሰለት፡፡ \v 13 የሶርያው ንጉሥ፡- ‹‹እርሱ የሚገኝበትን ስፍራ ፈልጉ፤ እኔም ልኬ እማርከዋለሁ›› አላቸው፡፡ በዚህም ጊዜ ኤልሳዕ በዶታይን እንደሚኖር ተነገረው፡፡

1
06/14.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 14 ስለዚህ ንጉሡ በፈረሶችና በሠረገሎች የተጠናከረ ብዙ ሠራዊት ወደ ዶታይን ላከ፡፡ እነርሱም በሌሊት ደርሰው ከተማዪቱን ከበቡ፡፡ \v 15 በማግስቱም ማለዳ የኤልሳዕ አገልጋይ ከመኝታው ተነሥቶ ከቤት ሲወጣ፣ በፈረሶችና በሠረገሎች የታጀቡ የሶርያ ወታደሮች ከተማዪቱን መክበባቸውን አየ፡፡ ወደ ኤልሳዕም ተመልሶ:- ‹‹ጌታዬ ወዮ! ምን ማድረግ ይሻለናል? ሲል ጠየቀው፡፡ \v 16 ኤልሳዕም ‹‹አይዞህ አትፍራ፤ ከእነርሱ ጋር ከተሰለፈው ይልቅ ከእኛ ጋር የተሰለፈው ሠራዊት ይበልጣል›› አለው፡፡

1
06/17.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 17 ኤልሳዕም ‹‹እግዚአብሔር ሆይ! ማየት እንዲችል ዐይኖቹን ክፈትለት! ሲል ጸለየ፤ እግዚአብሔርም የኤልሳዕን አገልጋይ ዐይኖች ከፈተለት፤ በኮረብታው ብዙ የእሳት ፈረሶችና ሠረገሎች በኤልሳዕ ዙሪያ እንዳሉ ተመለከተ፡፡ \v 18 ሶርያውያንም ወደ እርሱ በወረዱ ጊዜ ኤልሳዕ እንዲህ ሲል ጸለየ፡- ‹‹እግዚአብሔር ሆይ! እነዚህ ሰዎች እንዲታወሩ አድርግ! እግዚአብሔርም ኤልሳዕ እንደ ጸለየው፣ ዐይኖቻቸው እንዲታወሩ አደረገ፡፡ \v 19 ከዚህም በኋላ ኤልሳዕ ሶርያውያንን፡- ‹‹መንገድ ተሳስታችኋል፤ የምትፈልጓት ከተማ ይህች አይደለችም፤ ይልቅስ ወደምትፈልጉት ሰው እኔ ልምራችሁ፣ ተከተሉኝ›› ብሎ ወደ ሰማርያ መራቸው፡፡

1
06/20.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 20 ወደ ሰማርያም በደረሱ ጊዜ ኤልሳዕ፡- ‹‹እግዚአብሔር ሆይ! እነዚህ ሰዎች ማየት እንዲችሉ ዐይኖቻቸውን ክፈት! ሲል ጸለየ፡፡ እግዚአብሔርም ዐይኖቻቸውን በከፈተላቸው ጊዜ በሰማርያ መካከል መሆናቸውን ተረዱ፡፡ \v 21 የእስራኤልም ንጉሥ ሶርያውያንን ባያቸው ጊዜ ‹‹ጌታዬ! ልግደላቸውን? ልግደላቸውን? ሲል ኤልሳዕን ጠየቀው፡፡

1
06/22.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 22 ኤልሳዕም ‹‹አይሆንም! እንኳን እነዚህን በሰይፍህና በቀስትህ የማረካቸውን ወታደሮች መግደል አይገባህም፤ ይልቅስ የሚበሉትንና የሚጠጡትን ምግብ አቅርብላቸውና ወደ ንጉሣቸው ተመልሰው እንዲሄዱ አድርግ›› አለው፡፡ \v 23 ስለዚህም የእስራኤል ንጉሥ ለእነርሱ ታላቅ ግብዣ አደረገላቸው፤ ከበሉና ከጠጡም በኋላ ወደ ሶርያ ንጉሥ መልሶ ላካቸው፤ ከዚያም ጊዜ ጀምሮ ሶርያውያን በእስራኤል ምድር ላይ ወረራ ማድረጋቸውን አቆሙ፡፡

1
06/24.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 24 ከዚህ በኋላ የሶርያ ንጉሥ ቤን ሀዳድ መላ ሠራዊቱን ሰብስቦ በእስራኤል ላይ በማዝመት ጉዳት አደረሰ፤ የሰማርያን ከተማም ከበበ፡፡ \v 25 ስለዚህ በሰማርያ ጽኑ ራብ ነበር:: ከዚህም የተነሣ የአንድ አህያ ራስ ሰማኒያ መክሊት ብር፣ ሁለት መቶ ግራም የሚያህል የርግብ ኩስ ዋጋ እስከ አምስት መክሊት ብር ይሸጥ ነበር፡፡ \v 26 አንድ ቀን የእስራኤል ንጉሥ በከታማዪቱ የቅጥር ግንብ ላይ በሚመላለስበት ጊዜ አንዲት ሴት:- ‹‹ንጉሥ ሆይ እባክህ እርዳኝ! ስትል ጮኸች፡፡

View File

@ -113,6 +113,12 @@
"06-06", "06-06",
"06-08", "06-08",
"06-10", "06-10",
"06-12",
"06-14",
"06-17",
"06-20",
"06-22",
"06-24",
"07-title", "07-title",
"08-title", "08-title",
"09-title", "09-title",