am_2co_text_ulb/03/01.txt

1 line
771 B
Plaintext

\c 3 \v 1 ራሳችንን እንደገና ልናወድስ እንጀምራለንን? አንዳንድ ሰዎች እንደሚያደርጉት ለናንተም ሆነ ከእናንተ የድጋፍ ደብዳቤ ያስፈልገን ይሆን? አያስፈልገንም። \v 2 እናንተ ራሳችሁ በልባችን ላይ የተፃፋችሁ፥በሁሉም ሰዎች የምትታውቁ እና የምትነበቡ የድጋፍ ደብዳቤያችን ናችሁ። \v 3 በእኛ የቀረባችሁ የክርስቶስ መልዕክት ከመሆናችሁም በላይ በህያው የእግዚአብሔር መንፈስ እንጂ በቀለም ያልተፃፋችሁ፤በሰዎች የልብ ፅላት ላይ እንጂ በድንጋይ ፅላት ላይ ያልተቀረፃችሁ ናችሁ።