|
\v 5 ወደ መቄዶንያ በመጣን ጊዜ ሰውነታችን እረፍት አልነበረውም። ይልቁንስ በውጭ ግጭት እና በውስጥ ፍርሃት ስለነበረብን በሁሉ አቅጣጫ ተጨነቅን ። \v 6 ነገር ግን ተስፋ የቆረጡትን የሚያፅናና አምላክ በቲቶ መምጣት አፅናናን። \v 7 የእርሱ መምጣት ብቻ ሳይሆን እናንተም እርሱን ያፅናናችሁት ማፅናናት እኛን አፅናናን። ለእኔም ያላችሁን ታላቅ ፍቅር፥ርህራሄ እና ጥልቅ ሃሳብ ሲነግረን በይበልጥ ተደሰትሁ። |