am_2co_text_ulb/07/11.txt

1 line
933 B
Plaintext

\v 11 እግዚአብሔር የሚወደው ሃዘን ምን አይነት ታላቅ ቁርጠኝነት እንዳመጣላችሁ እዩ። ይህም ታላቅ ቁርጠኝነት ምን ያህል ንፁህ መሆናችሁን፥ ምን ያህል በሃጢያት ላይ እንድትቆጡ እንዳደረጋችሁ፥ ምን አይነት ናፍቆት እንዳሳደረባችሁ፥ ምን አይነት በጎ ቅንዓት እንደፈጠረባችሁ ፥ፍትህ እንድታደርጉም ምን አይነት ጥልቅ መሻት እንዳደረገላችሁ ተመልከቱ! በዚህ በኩል በሁሉም ንፁህ መሆናችሁን አስመስክራችኋል። \v 12 ምንም እንኳ ብፅፍላችሁም የፃፍኩት ለክፉ አድራጊ ወይም በክፉ አድራጎቱ መከራ ለሚቀበል ሳይሆን ለእኛ ምን ያህል እንደምታስቡ በእግዚአብሔር ፊት እንዲታወቅ ነው።