\v 16 ልክ እንደዚህ፣ እኔ አልከበድሁባችሁም፤ነገር ግን በጣም በተንኮልና በጥበብ ያታለልኃችሁ መሰላችሁ። \v 17 ወደ እናንተ በላክሁት በማንም ተጠቀምሁባችሁን? \v 18 ወደ እናንተ እንዲመጣ ቲቶን የግድ አልኩት ፤ ከእርሱ ጋርም ሌላውን ወንድም ላክሁት። ቲቶስ ተጠቀመባችሁን? በአንድ መንገድ አልተጓዝንምን? በአንድ ፈለግስ አልተራመድንምን?