\v 8 መውጊያውን ከእኔ እንዲያነሣው ሦስት ጊዜ ጌታን ለመንሁ። \v 9 እርሱም፣ « ጸጋዬ ይበቃሃል ኃይል በድካም ይፈጸማልና» አለኝ። ስለሆነም የክርስቶስ ኃይል ያርፍብኝ ዘንድ አብዝቼ ስለ ድካሜ እመካለው። \v 10 ስለዚህ ስለ ክርስቶስ በድካም፣ በስድብ፣ በችግር፣ በስደት ፣ በጭንቀትም እርካታ ይሰማኛል በምደክምበት ጊዜ ሁሉ ብርቱ ነኝና።