am_2ch_text_ulb/02/04.txt

1 line
680 B
Plaintext

\v 4 እነሆ በእግዚአብሔር ፊት የጣፋጩን ቅመም ሽታ ለማጠን፥ የመገኘቱን ኅብስት ዘወትር ለማኖር፥ በጠዋትና በማታ፥ በሰንበታቱም ፥ በመባቻዎቹና ለአምላካችን ለእግዚአብሔር በተመደቡት ልዩ በዓላት የሚቃጠለውን መሥዋዕት ለማቅረብ ለአምላኬ ለእግዚአብሔር ስም ቤት ልገነባና ልቀድሰው ነው፡፡ ይህ ለእስራኤል ለሁልጊዜ ሕግ ነው፡፡ \v 5 አምላካችን ከአማልክት ሁሉ በላይ ታላቅ ስለሆነ የምሠራው ቤት እጅግ ታላቅ ይሆናል፡፡