am_2ch_text_ulb/18/17.txt

1 line
523 B
Plaintext

\v 17 በመሆኑም የእስራኤል ንጉሥ ለኢዮሳፍጥ ፦" እኔን በተመለከተ ጥፋት ብቻ እንጂ መልካም ትንቢት እንደማይናገርልኝ አልነገርኩምን?" አለው፡፡ \v 18 ከዚያም ሚክያስ፦" እንግዲህ ሁላችሁም የእግዚአብሔርን ቃል መስማት ይገባችኋል፤ እግዚአብሔር በዙፋኑ ተቀምጦ የሰማይም ሰራዊት ሁሉ በቀኙና በግራው ቆመው እንደነበር አየሁ፡፡