am_2ch_text_ulb/18/15.txt

1 line
553 B
Plaintext

\v 15 ከዚያም ንጉሡ ፦" በእግዚአብሔር ስም ከእውነቱ በቀር ሌላ ምንም ነገር እንዳትነግረኝ ስንት ጊዜ እንድትምል ላደርግህ ይገባኛል?" አለው፡፡ \v 16 ሚክያስም፦" እስራኤል ሁሉ እረኛ እንደሌላቸው በጎች በተራሮች ላይ ተበትነው አየኋቸው፤ እግዚአብሔርም፦ 'እነዚህ እረኛ የላቸውም፡፡ እያንዳንዱ ሰው በሰላም ወደ ቤቱ ይመለስ' አለ" ብሎ ተናገረ፡፡