am_2ch_text_ulb/02/08.txt

1 line
823 B
Plaintext

\v 8 አገልጋዮችህ እንጨት ከሊባኖስ መቁረጥ እንደሚያውቁ ስለማውቅ ከሊባኖስ የዝግባ እንጨቶች፥ የጥድ እንጨቶች፥ የሰንደልም እንጨቶች ላክልኝ፡፡ እነሆ ባሪያዎችህ ከባሪያዎቼ ጋር ይሆናሉ፡፡ \v 9 ልሠራ ያሰብኩት ቤት ታላቅና ድንቅ ይሆናልና የተትረፈረፈ ሳንቃ እንጨት እንዲያዘጋጁልኝ ነው፡፡ \v 10 እነሆ እንጨቱን ለሚቆርጡ ሰዎች ሀያ ሺህ የቆሮስ መስፈሪያ የተፈጨ ስንዴ፥ ሀያ ሺህ የቆሮስ መስፈሪያ ገብስ፥ ሀያ ሺህ የባዶስ መስፈሪያ የወይን ጠጅ፥ ሀያ ሺህ የባዶስ መስፈሪያ ዘይት ለባሪያዎችህ እሰጣለሁ፡፡