am_2ch_text_ulb/02/06.txt

1 line
818 B
Plaintext

\v 6 ነገር ግን መላው አጽናፈ ዓለምና ሰማይ ራሱ ሳይቀር ሊይዘው ለማይችለው ለእርሱ ለእግዚአብሔር ቤት ይሠራ ዘንድ የሚችል ማን ነው? በፊቱ መሥዋዕት ከማቅረብ በስተቀር ለእርሱ ቤት እሰራ ዘንድ እኔ ማን ነኝ? \v 7 በመሆኑም በወርቅ፥ በብር፥ በናስ፥ በብረት፥ እንዲሁም ሐምራዊውን፥ ቀዩን፥ ሰማያዊውን ግምጃ በመሥራት የተካነ ሰው፥ የእንጨት ቅርጻ ቅርጽ ዓይነቶችን ሁሉ መሥራት የሚያውቅ ሰው ላክልኝ፡፡ እርሱም አባቴ ዳዊት ካዘጋጃቸው በእኔ ዘንድ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ካሉት የተካኑ ሰዎች ጋር ይሆናል፡፡