am_2ch_text_ulb/05/11.txt

1 line
704 B
Plaintext

\v 11 ካህናቱም ከቤተ መቅደሱ ቅዱስ ስፍራ ወጡ፡፡ በዚያ የነበሩትም ካህናት በተመደቡበት ክፍል ላይ ሳያተኩሩ ሁሉም ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ቀድሰው ነበር፡፡ \v 12 መዘምራን የነበሩትም ሌዋውያንም አሳፍን፥ ኤማንን፥ ኤዶታምን ልጆቻቸውንና ወንድሞቻቸውን ጨምሮ ሁሉም ጥሩ በፍታ ለብሰው ጸናጽል፥ በገና እና መሰንቆ/ክራር እየመቱ በመሠዊያው አጠገብ በስተምሥራቅ ቆመው ነበር፡፡ ከእነርሱም ጋር መቶ ሃያ መለከት የሚነፉ ካህናት ነበሩ፡፡