am_2ch_text_ulb/34/04.txt

1 line
666 B
Plaintext

\v 4 ሕዝቡ የበኣሊምን መሠዊያዎች በእርሱ ፊት አፈረሱ፤ እርሱ ከበላያቸው የነበሩትን የዕጣን መሠዊያዎች ሰባበረ። የማምለኪያ ዐፀዶቹንም ሰባበረ፤ የተቀረጹትን ምስሎች፥ ቀልጠው የተሠሩትንም ምስሎች አፈር እስኪሆኑ ድረስ አደቀቃቸው። ትቢያውንም መሥዋዕት ይሰዉላቸው በነበሩ ሰዎች መቃብር ላይ በተነው። \v 5 የካህናቶቻቸውንም አጥንቶች በመሠዊያቸው ላይ አቃጠለ። በዚህ መንገድ ይሁዳንና ኢየሩሳሌምን አጸዳ።