am_2ch_text_ulb/31/11.txt

1 line
868 B
Plaintext

\v 11 ከዚያም ሕዝቅያስ በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ መጋዘኖች እንዲዘጋጁ አዘዘ፤ እነርሱም አዘጋጇቸው። \v 12 ሥጦታዎቹን፥ አሥራቱንና የእግዚአብሔር የሆኑትን ነገሮች በታማኝነት አመጡ። ሌዋዊው ኮናንያ የበላያቸው አስተዳዳሪ ነበር፤ ወንድሙም ሰሜኢ በደረጃ ከእርሱ ቀጥሎ ሁለተኛ ነበረ። በንጉሡም በሕዝቅያስና በእግዚአብሔር ቤት ላይ ባለ ሥልጣን በነበረው በዓዛርያስ የተሾሙ፥ ከኮናንያና ከወንድሙ ከሰሜኢ እጅ በታች \v 13 ይሒዒል፥ ዓዛዝያ፥ ናሖት፥ አሣኤል፥ ይሬሞት፥ ዮዛባት፥ ኤሊኤል፥ ሰማኪያ፥ መሐት፥ በናያስ አስተዳዳሪዎች ነበሩ።